በእውነቱ የት እንዳላችሁ፤ እነማን እንደሆናችሁ፤
ስንት እንደሆናችሁና ምን እንደምትፈልጉ ባናውቅም ያልጻፋችሁትና ያልደረሰን ደብዳቤአችሁ እንዲያው በደፈናው ደርሶናል።
ካልታወቁና በደፈናው ሩቅ ምሥራቆች ጽፈው የላኩት ደብዳቤ ደርሶናል እንዴት ትላላችሁ? ብላችሁ ብትጠይቁን መልሳችን፤ በዘንድሮው
ሲኖዶስ ያቀድነውና የጎነጎንነው ሁሉ ስላልተሳካ በዓለም የሚገኘው ምእመን ሁሉ በአዲስ አበባ «ታህሪር» አደባባይን እንዲፈጥር የሀገር
ውስጡን ሕዝብ ሞራል ለመገንባት የምንጠቀምበት ስልት እንጂ በእርግጥ ከላይ የጠየቃችሁትን ዓይነት ግምት ስናስብ ከምዕራብም ይሁን
ከምሥራቅ፤ ከደቡብ ይሁን ከሰሜን የተላከ ምንም ዓይነት የአድማ ደብዳቤ እስካሁን እጃችን አልገባም። ደብዳቤዎቹን እኛው በቢሮአችን
እያረቀቅን፤ አቅጣጫ እያወጣንለት በግለሰብም ይሁን በጉባዔዎች ስም የምንጽፈው ራሳችን እንደሆንን እንድታውቁልን እንፈልጋለን።
ከላይ የተጻፈውን
ያልነው «ደጀ ሰላም» ብሎግ ከሩቅ ምሥራቅ መጣልኝ በማለት ያወጣውን ንባብ ካየነው በኋላ የገባበትን ጭንቀት በመጋራት የሩቅ ምስራቁን
ደብዳቤ ግልጽ ለማድረግ ፈልገን እንጂ ለእኛ ብሎግ ከሩቅ ምሥራቅ የደረሰን የፈጠራ ደብዳቤ ኖሮ አይደለም።
«ደጀ ሰላም» ብሎግ ከጥላሁን ገሠሠ ዓለማዊ ዘፈን
ጋር ወዳጅነት የያዘ መስሏል። ወደ ሩቅ ምሥራቅ ሄዶ «ጃፓኗን ወድጄ» እያለ ከሩቅ ምሥራቅ ተላከልኝ የሚለውን የፍቅር ደብዳቤ በገጹ
ጽፎ አስነብቦናል። ሩቅ ምሥራቅ ማለት ጃፓንና አካባቢዋ ያሉ ሀገሮች ናቸው።
የማቅ አፈቀላጤ «ደጀ ሰላም» ስንት ቆንጆዎችን ከወደ ሩቅ ምሥራቅ እንዳፈራ
ለጊዜው ባናውቅም እሱ ግን የተላከለትን «ውዴ አንተ ነህ፤ ዶ/ር መስፍን ውዴ ነው፤እኔም የአንተ ውድ ነኝ» የሚል ደብዳቤ ደርሶኛል
ሲል ያቀረበውን ደብዳቤ ተመልክተን በመግቢያችን ላይ ያልተላከ ደብዳቤ
ተላከ ለማለት ተገደድን።
«አዎ የማናውቃችሁ ሩቅ ምሥራቆች ያልተላከው ደብዳቤአችሁ
ደርሶናል» በማለት!!
«ደጀ ሰላም» ብሎግ ከሌሎቹ የዓለም ማእዘን ተጻፈልን
ሲል እንደቆየው ሁሉ አሁን ደግሞ ከቀረው ሩቅ ምሥራቅ ለአንዴና ለመጨረሻ
ጊዜ እድሉን ለመጠቀም ደብዳቤውን ራሱ ጽፎ ወይም በዶ/ር መስፍን
አስጽፎ ሲያበቃ ከሩቅ ምሥራቅ የደረሰኝ ነው ሲል ብሎጉ ላይ በመለጠፍ ሰውን ሁሉ እንደጅል ሊያጃጅል ይሞክራል።