ማቅ ስንቱን ደብድቧል፤ አስደብድቧል፤ ከሀገር
አስወጥቷል፤ የስንቱንስ ኃጢአት አዋጅ ነግሯል፤ አስነግሯል፤ በንግድ ጋዜጣው ላይ ሰዎች በሥጋ ድካም የሰሩትን አበሳ ስንት ገጽ
ጽፏል?ብለን ብንጠይቅ የሚችለውንና የሮጠውን ዘመን ሁሉ ሲያደርግ
ቆይቷል።
እውነት ማቅ መልካም ስለሰራ ነው ወይ የተጠላው?
ለቤተክርስቲያንስ ስለቆመ ነው? የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ሁሉ ዓይንህን ላፈር የሚሉት? እውነት መንግሥት ለሥልጣኑና ለአገዛዙ የማመቸው ማኅበር እንደሆነ አያውቅም? ሲኖዶስ በእሱ እጅ እየታመሰ እንደቆየ እኛስ አንረዳም? በአሜሪካ ይሁን በአዲስ አበባ፣ በሰንበት ት/ቤቶች ጉባዔ ይሁን በሰንበቴው ማኅበር ማቅ እጁ የሌለበት ቦታ አለ?ብለን ብንጠይቅ እስከዛሬ ለዘራው ሁሉ ሰዓቱ ሲደርስ አሁን የቅጣት አዝመራውን እያፈሰ ነው እንላለን።
ከጥቂት አለቅላቂዎች በስተቀር ካህናቱ ሁሉ እንደጭራቅ
የሚመለከቱት እንደሆነ ይታወቃል። መንግሥት አሸባሪ ነህ ብሎታል። በዘንድሮው ሲኖዶስ ተላላኪ አባላቱ እንኳን የዚህ ሽብር ቡድን ገመና
መሸፈን አልቻሉም። እንኳን ያንን ያህል ተራምደው እንደድሮው ሊታደጉት ይቅርና የራሳቸውን የጥፋት ክንብንብ ባለበት ሸፍነው ማቆየት አልቻሉም። መ/ምስጢር ወ/ሩፋኤልና ካህሳይ ገ/እግዚአብሔር ሽፋናቸውን በፍትህ
መንፈሳዊ ገጸ ንባብ እየገለጡ አደባባይ ላይ አሰጧቸው። በዜና ቤተክርስቲያን ገመና ገላጭነት ላይ 3 ቀናት ጉባዔ ተቀምጠው አንዴ
ይቅረቡ፤ አንዴ ደግሞ ኰሚቴ ይቋቋም፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይወገዙ፤ ሲጨንቃቸው ደግሞ ንብረት የለኝም ወዘተ የሚል ሰበብ በመፍጠር «የባሰበት እመጫት» ያገባል እንዲሉ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ሲቆርጡና ሲቀጥሉ
ሰንብተው ማቅን ከገባበት አጣብቂኝ ማውጣት አልቻሉም ብቻ ሳይሆን የራሳቸውም አጣብቂኝ አስጨንቋቸዋል።