- ሕገ ቤተ ክርስቲያናችን ከየት ወዴት
- የደጀ ሰላም ቁጣ
- ምንጭ፤ዐውደ ምሕረት ብሎግ
ደጀ ሰላም ከዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዝግጅት ጀርባ በሚል ርዕስ በጻፈው ዘገባ በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ላይ ያለውን ምሬት ገልጧል፡፡ እንዲያውም
ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ “እኔ ማንንም አልፈራም፤ ጽሑፉ አያስጠይቀኝም እንጂ ብጠየቅበት አልፈራም፤ በይዘቱ አዲስ አይደለም፤ የተለያዩ ግለሰቦች በየራሳቸው አቀራረብ ሲጽፉት የቆዩት ነው፤ እኔ ለመጻፍ የሞከርኹት የቤተ ክርስቲያን ህልውና እየተነካ ነው ብዬ በማምንበት ስለ ጳጳሳት ንብረት ጉዳይ ነበር፤ አባ ጳውሎስ ግን በሲኖዶስ ስብሰባ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይሻሻል አሉ፤ እውነቱን ለመናገር ግን ጽሑፉ ከውጭ የመጣ እንጂ በዝግጅት ክፍሉ የተጻፈ አይደለም፤ በስሜ እየተነገደብኝ ነው፤” ብለዋል፡፡ ሲል ዘግቧል፡፡
በዛሬው ዕለት የቀጠለው የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ በጋዜጣው ላይ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዞ የነበረ ሲሆን ዋና አዘጋጁና ምክትል ዋና አዘጋጁ ሳይቀርቡ ስብሰባውን መቀጠሉ ታውቋል፡፡
ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በርግጥ ይሄ ደጀ ሰላም ያወጣውን ዘገባ ተናግረዋልን? የሚለው ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ በቅዳሜው ዕለት ስብሰባ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅና ምክትል አዘጋጁ ይቅረቡልኝ ብሎ ያዘዘው ሲኖዶስ ለምን ዛሬ እነርሱ ሳይቀርቡ ስብሰባውን ለማድረግ ፈለገ? የሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት መሞከር ተገቢ ነው፡፡