Monday, May 14, 2012

ቤተክርስቲያንንና መንጋዎቿን ከወቅታዊ አደጋ ለመታደግ ከግንቦቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚጠበቅ የህልውና ውሳኔ

  • ሕገ ቤተ ክርስቲያናችን ከየት ወዴት
  • የደጀ ሰም ቁጣ
  •                         ምንጭ፤ዐውደ ምሕረት ብሎግ
ደጀ ሰላም ከዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ዝግጅት ጀርባ በሚል ርዕስ በጻፈው ዘገባ በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ላይ ያለውን ምሬት ገልጧል፡፡ እንዲያውም  ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒእኔ ማንንም አልፈራም፤ ጽሑፉ አያስጠይቀኝም እንጂ ብጠየቅበት አልፈራም፤ በይዘቱ አዲስ አይደለም፤ የተለያዩ ግለሰቦች በየራሳቸው አቀራረብ ሲጽፉት የቆዩት ነው፤ እኔ ለመጻፍ የሞከርኹት የቤተ ክርስቲያን ህልውና እየተነካ ነው ብዬ በማምንበት ስለ ጳጳሳት ንብረት ጉዳይ ነበር፤ አባ ጳውሎስ ግን በሲኖዶስ ስብሰባ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይሻሻል አሉ፤ እውነቱን ለመናገር ግን ጽሑፉ ከውጭ የመጣ እንጂ በዝግጅት ክፍሉ የተጻፈ አይደለም፤ በስሜ እየተነገደብኝ ነው፤ብለዋል፡፡ ሲል ዘግቧል፡፡

 በዛሬው ዕለት የቀጠለው የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ በጋዜጣው ላይ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዞ የነበረ ሲሆን ዋና አዘጋጁና ምክትል ዋና አዘጋጁ ሳይቀርቡ ስብሰባውን መቀጠሉ ታውቋል፡፡
ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በርግጥ ይሄ ደጀ ሰላም ያወጣውን ዘገባ ተናግረዋልን? የሚለው ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ በቅዳሜው ዕለት ስብሰባ የጋዜጣው ዋና አዘጋጅና ምክትል አዘጋጁ ይቅረቡልኝ ብሎ ያዘዘው ሲኖዶስ ለምን ዛሬ እነርሱ ሳይቀርቡ ስብሰባውን ለማድረግ ፈለገ? የሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት መሞከር ተገቢ ነው፡፡

ማቅ በደጀ ሰላም ብሎግና በፍትህ ጋዜጣ ላይ የጽሁፍ ዘመቻውን ቀጥሏል!

እንደሚታወቀው የቆንጆዎችና የዓለመኞች ኢንተርቴይንመንት ማስታወቂያ በሆነችው «ዕንቁ»  መጽሔት ላይ ጭቃ ጅራፉን ሲያጮህ እንደቆየው ሁሉ  ዛሬ ደግሞ የሲኖዶስ ጉባዔ ሲቃረብ  ጽሁፎቹን ሀገር ውስጥ ላሉ ለጋዜጦች እየላከ «አቶ ሽብሩ/ ማቅ » ዘመቻውን እያጧጧፈ ይገኛል። እንግዲህ ይሄ በአንድ ወገን በኢንተርኔቱ አፈ ቀላጤው «ደጀ ሰላም» በኩል የሚያሰራጨው ዲስኩር ላልደረሰው ተከታይ፤ በህትመት ውጤት በኩል እንዲደርሰው ያቀደው ሌላኛው መላ መሆኑ ነው። ምንም እንኳን ማንም ሰው በመሰለው የሚዲያ መንገድ ሃሳብን በነጻ መግለጽ መብቱ መሆኑ ባይካድም ተመሳሳይ ጽሁፍ በተለያየ ሚዲያ ላይ ሲወጣ ጽሁፉ የራሱ መሆኑን በስሙ ወይም ከሌላ ቦታ ያገኘው ከሆነም ያገኘበትን ምንጭ መጥቀስ የተገባው መሆኑ ከጥያቄ የሚገባ ጉዳይ አይደለም።  ይሁን እንጂ በእጅ አዙር አሰራር የተካኑ አባትና ልጁ «ደጀ ሰላም» በብሎግ  ያወጣውን  ጽሁፍ «ፍትህ» በተሰኘው የግል ጋዜጣ ላይ ምንም ሳይጨመርበትና ሳይቀነስበት እንዳለ ተጽፎ አግኝተናል። ደጀ ሰላምም የራሱ እንደሆነ በስሙ ሲያወጣ «ፍትህ» ጋዜጣም ያንኑ ጽሁፍ ከደጀ ሰላም ብሎግ ያገኘው መሆኑን ሳይናገር ለህትመት አብቅቷል። አንድ ዓይነት ጽሁፍ ባንድ ጊዜ እንዴት የተለያዩ ወገኖች ባለቤት ሊሆን ይችላል?  የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ የግድ ነው። እስከሚገባን ድረስ «ደጀ ሰላም» እና «ፍትህ» ጋዜጣ አንድ ተቋም በባለቤትነት የሚመራቸው እንዳልሆነ ነው። ምናልባት ከኋላ ሆኖ መረጃውን እያጠናቀረ ሁለቱንም ሚዲያ የሚመግብና የሚልክላቸው ስውር እጅ አለ ብለን ብንገምት  ግምታችን ከእውነት የራቀ አይሆንም። ምክንያቶቹን እስኪ እንመልከት።

Sunday, May 13, 2012

(ርእሰ አንቀጽ) የአባቶች ገበና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ሲጋለጥ!

(በትናንትናው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶሱ በሰበር ያስተናገደው አጀንዳ በዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ የተጻፈ ርዕሰ አንቀጽን የተመለከተ ነው። ርዕሰ አንቀጹ ለምን አወያየ? የሚለው በብዙዎች ዘንድ መወያያ ስለሆነ ርዕስ አንቀጹን እንዳለ አቅርበነዋል። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ)
                          ምንጭ፤ዐውደ ምሕረት
            « የዜና ቤተክርስቲያንን» ከፊል ዘገባ ለመመልከት ( እዚህ ይጫኑ)
ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት፣ የካህናትና የምእመናን ድምር ውጤት ናት፤ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን ባልን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ማለታችን ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ብለን በጥቅሉ በምንናገርበትም ጊዜ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን ማለታችን ነው፡፡ በአጠቃላይ እነዚህ ሁሉ አካላት የተካተቱባት ቤተ ክርስቲያን አንዲት ተቋም ስለሆነችም ማኅበር ተብላ ትጠራለች፤ ራሷ ማኅበር ስለሆነችም ከዝክርና ከሰንበቴ ማኅበር በስተቀር በተቋም የተደራጀ ሌላ ማኅበር አያስፈልጋትም፡፡
ሆኖም ቤተ ክርስቲያናችን ቃለ ዓዋዲ የተሰኘ የመተዳደሪ ደንብ አውጥታ በሰበካ ጉባኤ ከመደራጀቷ በፊት የእርሷ ወኪልና ደጋፊ በመሆን ድምፅ የሚያሰሙላት አንድ አንድ የወጣት መንፈሳውያን ማኅበራት እንደነበሩ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ በሰበካ ጉባኤ ከተደራጀች ወዲህ ግን ሕገ ልቡና እስከ ሕገ ኦሪት፤ ሕገ ኦሪትም እስከ ሕገ ወንጌል መዳረሻ ሆነው ወይም አገልግሎት ሰጥተው እንዳለፉ ሁሉ እነሱም አልፈዋል፡፡ ይህም ማለት በቃለ ዓዋዲው የመተዳደሪያ ደንብ በየድርሻቸው ተካትተዋል ማለት እንጅ ጨርሰው ወድመዋል ማለት አይደለም፡፡
ቤተ ክርስቲያን የምትመራበትና የምትተዳደርበት ሕገ ቤተ ክርስቲያን ወይም ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ሕገ ቤተ ክርስቲያን በዘመነ ሐዋርያት በቅዱሳን ሐዋርያት የተደነገገ ሕግ ሲሆን በመላው ዓለም የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሚመሩትና የሚተዳደሩት በዚሁ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት አካል እንደመሆኗ መጠን የምትመራውና የምትተዳደረው ወይም የምትዳኘው ከፍ ሲል በሕገ ቤተ ክርስቲያን፤ ዝቅ ሲል በቃለ ዓዋዲ የመተዳደሪያ ደንብ ነው፡፡