የጽሁፉ ምንጭ፦አውደ ምህረት
ብፁዕ
አቡነ አብርሃም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከምእመናን ተለምኖ በተገኘ ገንዘብ የተገዛውን የዲ.ሲ. እና አካባቢው መንበረ ጵጵስና ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወሰነ። ማኅበረ ቅዱሳን እያለ ራሱን በሚጠራው ድርጅት አቀንቃኝነታቸው የሚታወቁት ወጣቱ ጳጳስ አቡነ አብርሃም በአሜሪካ በተለያየ ስቴቶች በተካሄዱ ጉባዔያት አማካይነት ከምእመናን በተሰበሰበ የአሜሪካ ዶላር 265 000.00 የተገዛው መንበረ ጵጵስና በራሳቸው እና በወሮ. ሀረገወይን ስም ለምን ለማዛወር እንደፈለጉ ባይታወቅም መንበረ ጵጵስናው የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ንብረት መሆኑ እየታወቀ አላስረክብም ማለታቸው በዘመናዊ አነጋገር ”የመርካቶ ቁጩ” ዐይነት ቢሆንም የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግሥታት እንዲያውቁት ተደርጎ በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ ከዚህ በታች አባሪ በሆነው ደብዳቤ መታዘዛቸውን ቤተ ክርስቲያን ገለጸች።
ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ(ጽሁፉን አሳድገው ያንብቡ)
መቼም
መስከረም ሳይጠባ … እንደሚባለው የዋሽንግተንና አካባቢዋ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል መንበረ ጵጵስናውን በሥርዐት እንዲያስረክቡ በተደጋጋሚ ቢጽፍላቸውም አሻፈረኝ ብለው መንበረ ጵጵስናውን ለማኅበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት (ደጀ ሰላምና አሃቲ ተዋህዶ ብሎግ ማዘጋጃ) አከራይተው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ታውቁዋል። እኒህ ጳጳስ እንደሚታወቀው ቀደም ሲል ከመርካቶው ራጉኤል ቤተ ክርሰቲያን ባካበቱት (በዘረፉት ቢባልም ሥራቸው ነውና ራሳቸው ይፈሩ!) ገንዘብ ሲ.ኤም.ሲ. አጠገብ ፎቅ ቤታቸውን ሠርተው ሳያፍሩ ያስመረቁ ሲሆን፣ በቅርቡም በባንክ ሂሣብ የተጠራቀመውን ከዲ.ሲ ከወሰዱት የሀገረ ስብከቱ ገንዘብ እና አቶ አሥራት የሚባል (የጎጃሙ ባለአውሊያ) የቸራቸውን ብር 400 000.00 በመጨመር ሁለት ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገንዘብ ልዩ ላንድ ክሩዘር ገዝተው ኢ-መንፈሳዊ የሆኑ ተግባራትን እያከናወኑበት ይገኛሉ።