Sunday, May 6, 2012

"ማኅበረ ቅዱሳን" በአርቤጎና ከተማ ጥዋ ማኅበራትን በአንድነት ስም ለመጨፍለቅ ያደረገው እንቅስቃሴ ተቃውሞ ገጠመው


                                     source:http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com
 "ማኅበረ ቅዱሳን" በሲዳማ፣ ጌዴኦ፣ አማሮና ቡርጂ ሀገረ ስብከት፣ በአርቤጎና ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሥር ያሉትን ልዩ ልዩ የጥዋ ማኅበራትን በአንድ ጥላ ሥር ለማደራጀት ሙከራ ቢያደርግም ተቃውሞ እንደተነሳበት ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የጥዋ ማኅበራት መመሥረትና መደራጀት እንዲሁም የምዕመናን መሰባሰብ እንደጦር የሚያስፈራው "ማኅበረ ቅዱሳን" በተለያዩ ፃድቃን፣ ሰማዕታትና መላዕክት ስም የተመሠረቱትን የጥዋ ማኅበራት በማፍረስ እንቅስቃሴ መጠመዱን በተጨማሪ የደረሰን መረጃ ያሰረዳል፡፡

የአርቤጎና ከተማ አማንያን በተለያዩ የጥዋ ማኀበራት ተደራጅተው ለዘመናት የቆዩ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንድ ተደራጁ የሚለው "ማኅበረ ቅዱሳን" መመሪያ በከፍተኛ መደናገር ውስጥ እንደከተታቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" የጥዋ ማኅበራትን ለመጨፍለቅ ሙከራ ሲያደርግ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም ያሉ ወገኖች እንዳስረዱት፣ ቀደም ሲል በሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ገብርኤል ገዳምም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ አድርጎ የከሸፈበት መሆኑ በተጨማሪ ታውቋል፡፡ በገዳሙ እሰከ 40 የሚደርሱ የጥዋ ማኅበራት የሚገኙ ሲሆን በቅድስት አርሴማ፣ በኪዳነ ምሕረት፣ በቅዱስ ገብርኤል እና በቅዱስ ሚካኤል ስም ብቻ እስከ አሥር፣ አሥር የሚደርሱ የጥዋ ማኅበራት ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች የጥዋ ማኅበራትም ተደራጅተው በእህትማማችና በወንድማማች መንፈስ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

Friday, May 4, 2012

«አሁን ደግሞ ገፍተው፤ ገፍተው ማንን ይሆን የሚወረውሩት?»

                                                                      (by dejebirhan)
አንድ ሰሞን የዘመድኩን በቀለ ትኩሳት  «በደጀሰላምና አንድ አድርገን» እንዲሁም በሌሎቹ ውርንጭላ ብሎጎች ሳይቀር፤  ይሄ ነው የተዋህዶ ልጅ፣ ሲኦልም ቢሆን ግባ፤ ውረድ ፣ ዘመድኩን  የአባ ቢላዋ ልጅ፣ ቆራጡ፤ እሳቱ፤ አንድ ለእናቱ፤ ጀግናው ፣ ሰማእቱ ምኑ ቅጡ፤ ያልተባለ፣ ያልተወራ ነገር አልነበረም። ከወሬ አቀባባዮቹ ብሎጎች አንስቶ፤ የወሬ አቀባባዮቹ አስተያየት ሰጪዎች ሁላቸውም በአንድነት፤ በአንድ ጀምበር ዘመድኩንን አጽድቀው፣ እነሱንም የሰማእትነት ሲቃ በሚተናነቃቸው  አስተያየቶች ተዥጎድጉደው ድረ ገጾቹን በእንቶ ፈንቶ አቆሽሸው ዘመድኩንን ከእርቅ አጣልተው ሲያበቁ ለተመኙለት   የእነሱ  ሲኦል (በኛ በኩል ግን እስር ቤት) ዱለውት ሲያበቁና  ፋይሉ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት መልስ  ሲሆን አንድም አጨብጫቢ ቃሊቲ አብሮት ሳይወርድ ያ ሁሉ ጯሂ የራሱን ኑሮ ወደማሞቁ መመለሱን ታዝበን ተገርመናል፣ ምናልባትም ዘመድኩን ዛሬ ላይ ሆኖ የያኔውን ግፋ በለው ፤ዓይኑን ገልጦ ሲመለከት  ያን ሁሉ ጆፌ አሞራ እንደእኛው ታዝቦ  ምን እንደሚሰማው ስንገምት «ሰውን ማመን ቀብሮ ነው» በተለይም ማቅን ማመን ውሃ መጨበጥ ነው፤ ይል ይሆናል። ያም ሆነ ይህ ጥሩ የትምህርትና ነገሮችን የማመዛዘን ጊዜ እንደሚሆንለት አይጠረጠርም። በዚያ መጠቀም ሳይችል ቀርቶ በከሰሱኝ  ሰዎች ላይ ቂሜ አይበርድም በሚል  ስሜት  በቀል አርግዞ የሚወጣ ከሆነም ከርቸሌ ውስጥ በችግር ተወልውሎ በተዘጋጀ የልቡ አዳራሽ፤ ከደጅ ቆመው የሚጠብቁት የቂም መናፍስት ወዲያው ገብተው የከፋ ችግር ከሚያመጡበት በቀር እሱ የሚጎዳው ወይም የሚያመጣው አንዳች ነገር እንደማይኖር ከወዲሁ ማስገንዘቡ ተገቢ ነው። ለማንኛውም ቃሊቲ የማስተዋል፣ የመማርና የማገናዘብ ጊዜ እንዲሆንለት ምኞታችን ነው።

አንዳንድ የማቅ አባላት የሲ. አይ. ኤ. ሰላዮች ሆነው ተገኙ

በዋናነት ቤተ ክህነት አካባቢ “የቀን መጋኛ” የሚባለው ባያብል ሙላቱ የሰጠውን መረጃ ዊኪሊክስ ይፋ አድርጓል።   በዲ/ን ሙሉጌታ ወ/ገብርኤል
 

በይበልጥም የኬብል ቁጥር 
ADDIS ABAB 00000451  002 OF 003  የሚለውን ይመልከቱ!!

 
በርካታ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ሌሎች ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት የተለያየ ነው። ማኅበሩ እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ በቅድሚያ ቤተክርስቲያንን ከዚያም የመንግስትን ሥልጣን ለመያዝ በግልጾቹም በስውሮቹም አመራሮች እየተደገፈ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን አባላቱ በቅጡ አልተረዱም። ቤተክርስቲያን እኛ ባንኖር ኖሮ ጠፍታ ነበር። ያለንላት እኛ ነን። ቤተክርስቲያን ሰው ስለሌላት አስራታችሁን ለማኅበረ ቅዱሳን አውጡ በማለት የሚያሰወራውን ወሬ  እና በአካፋ ተቀብሎ በማንኪያ የሚሰጠውን ስጦታ በማመን የተታለሉ ወገኖች ይገኛሉ። እውነቱን ከማህበሩ ጋር ለበርካታ አመታት በቅርብ የሰሩ ወገኖችና እንቅስቃሴውን በሙላት የተረዱ የቤተክርስቲያን ልጆች ያውቁታል።