(by dejebirhan)
አንድ ሰሞን የዘመድኩን በቀለ ትኩሳት «በደጀሰላምና አንድ አድርገን» እንዲሁም በሌሎቹ ውርንጭላ ብሎጎች ሳይቀር፤
ይሄ ነው የተዋህዶ ልጅ፣ ሲኦልም ቢሆን ግባ፤ ውረድ ፣ ዘመድኩን
የአባ ቢላዋ ልጅ፣ ቆራጡ፤ እሳቱ፤ አንድ ለእናቱ፤ ጀግናው ፣ ሰማእቱ
ምኑ ቅጡ፤ ያልተባለ፣ ያልተወራ ነገር አልነበረም። ከወሬ አቀባባዮቹ ብሎጎች አንስቶ፤ የወሬ አቀባባዮቹ አስተያየት ሰጪዎች ሁላቸውም
በአንድነት፤ በአንድ ጀምበር ዘመድኩንን አጽድቀው፣ እነሱንም የሰማእትነት ሲቃ በሚተናነቃቸው አስተያየቶች ተዥጎድጉደው ድረ ገጾቹን በእንቶ ፈንቶ አቆሽሸው ዘመድኩንን ከእርቅ
አጣልተው ሲያበቁ ለተመኙለት የእነሱ ሲኦል
(በኛ በኩል ግን እስር ቤት) ዱለውት ሲያበቁና ፋይሉ ተዘግቶ ወደ
መዝገብ ቤት መልስ ሲሆን አንድም አጨብጫቢ ቃሊቲ አብሮት ሳይወርድ
ያ ሁሉ ጯሂ የራሱን ኑሮ ወደማሞቁ መመለሱን ታዝበን ተገርመናል፣ ምናልባትም ዘመድኩን ዛሬ ላይ ሆኖ የያኔውን ግፋ በለው ፤ዓይኑን
ገልጦ ሲመለከት ያን ሁሉ ጆፌ አሞራ እንደእኛው ታዝቦ ምን እንደሚሰማው ስንገምት «ሰውን ማመን ቀብሮ ነው» በተለይም ማቅን ማመን
ውሃ መጨበጥ ነው፤ ይል ይሆናል። ያም ሆነ ይህ ጥሩ የትምህርትና ነገሮችን የማመዛዘን ጊዜ እንደሚሆንለት አይጠረጠርም። በዚያ መጠቀም
ሳይችል ቀርቶ በከሰሱኝ ሰዎች ላይ ቂሜ አይበርድም በሚል ስሜት በቀል
አርግዞ የሚወጣ ከሆነም ከርቸሌ ውስጥ በችግር ተወልውሎ በተዘጋጀ የልቡ አዳራሽ፤ ከደጅ ቆመው የሚጠብቁት የቂም መናፍስት ወዲያው
ገብተው የከፋ ችግር ከሚያመጡበት በቀር እሱ የሚጎዳው ወይም የሚያመጣው አንዳች ነገር እንደማይኖር ከወዲሁ ማስገንዘቡ ተገቢ ነው። ለማንኛውም ቃሊቲ የማስተዋል፣ የመማርና የማገናዘብ ጊዜ እንዲሆንለት ምኞታችን ነው።