በዋናነት ቤተ ክህነት አካባቢ “የቀን መጋኛ” የሚባለው ባያብል ሙላቱ የሰጠውን መረጃ ዊኪሊክስ ይፋ አድርጓል። በዲ/ን ሙሉጌታ ወ/ገብርኤል
በይበልጥም የኬብል ቁጥር
ADDIS ABAB 00000451 002 OF 003 የሚለውን ይመልከቱ!!
በርካታ
የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና ሌሎች ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት የተለያየ ነው። ማኅበሩ እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ በቅድሚያ ቤተክርስቲያንን ከዚያም የመንግስትን ሥልጣን ለመያዝ በግልጾቹም በስውሮቹም አመራሮች እየተደገፈ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎችን አባላቱ በቅጡ አልተረዱም። ቤተክርስቲያን እኛ ባንኖር ኖሮ ጠፍታ ነበር። ያለንላት እኛ ነን። ቤተክርስቲያን ሰው ስለሌላት አስራታችሁን ለማኅበረ ቅዱሳን አውጡ በማለት የሚያሰወራውን ወሬ እና በአካፋ
ተቀብሎ በማንኪያ የሚሰጠውን ስጦታ በማመን የተታለሉ ወገኖች ይገኛሉ። እውነቱን ከማህበሩ ጋር ለበርካታ አመታት በቅርብ የሰሩ ወገኖችና እንቅስቃሴውን በሙላት የተረዱ የቤተክርስቲያን ልጆች ያውቁታል።