ሙስሊሞች ሁሉ አክራሪዎች ወይም ክርስቲያን የተባሉ
ሁሉ ክርስቲያኖች ናቸው ብለን አናምን። ከሁለቱም ወገን ሃይማኖቱን ተጠግቶ የራሱን ገበያ የሚያደራና ስውር አጀንዳውን በሰው ላይ
ለመጫን የሚፈልግ እንዳለ የአደባባይ እውነታ ነው።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት የፓርላማ መግለጫ
ላይ በሁለት ወገን ስላሉት ሃይማኖታዊ ታዛውን የተጠለሉትን ኢትዮጵያውያን ችግር ፈጣሪዎችን ቀድሞውኑ ያወቅናቸው ቢሆንም የየግላችንን
ጩኸት ከረፈደ በኋላም ቢሆን በግልጽ አውጀው ነግረውናል።
የሚገርመው ነገር ከእስላሞቹ አሸባሪዎች ወገን
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ድምጽ ከንቱ ስሞታ ለማለት ጊዜ ያልፈጀባቸው ሲሆን እውነታው ግን በኢትዮጵያ ውስጥ አሸባሪነት ስለመኖሩ የኢትዮጵያው
ጠቅላይ ሚኒስትር ዲሞክራት ይሆኑ አምባ ገነን ከእሳቸው ሥርዓት ጋር ሊያያዝ የማይገባውን ነገር ለማያያዝ በመሞከር ግራና ቀኝ የተቃውሞ
ጅራፍ ማስጮህ በምድሪቱ ላይ ያለውን እውነታ የሚለውጠው አይደለም።