Sunday, April 29, 2012

አማኝ እንጂ አክራሪ አትሁን።

አማኝ ያመነውን የሚኖር በፍቅርም የሚማርክ ጀግና ነው። አክራሪ ግን ጥቂት እውቀቱን ከዱላ ጋር ለማስከበር የሚሞክር ነው። የከረረ ነገር መበጠሱ አይቀርም። የከረረ ነገር ሲከርም ሲበጠስም ስጋት ነው። አክራሪነት የአለሙ ልከኛ ሰው እኔ ነኝ። ከኔ በቀር በአለም ላይ ማንም መኖር የለበትም። ከምስራቅ ስገላበጥ ምእራብ እደርሳለሁ። ከሰሜን ስራመድ ባንድ ስንዝር ደቡብን እረግጣለሁ። ስለዚህ ከኔ ውጪ ማንም መኖር የለበትም ብሎ እንደማሰብ ነው። የአክራሪነት ምንጩ አለማወቅ ነው። አክራሪ ሰው በከሳሽነት መንፈስ የተያዘ እንጂ የሚያሳየው ማራኪ ስራ የሌለው ነው። ጥቂት እውቀቱ ከሰፋች የካደ ስለሚመስለው ላለማወቅ ተጠንቅቆ የሚጓዝ ነው። እርሱ ካለበት ገድጓድ ውጪ አለም ያለ የማይመስለው የለመድኩት ሰይጣን ይሻላል ብሎ ከመቃብር ጋር በኪዳን የሚኖር ተስፋ የሌለው ሳይሞት መኖር ያቆመ ሳይቀበር እውቀቱን የጨረሰ ሰው ነው። የአክራሪነት ወንድሙ አለማወቅ ነው። እኔ ያወቁት ብቻ ትክክል እኔ ከሰማሁት ውጪ ያለው ያተነገረ ነው አለም በኔ ጓዳ በኩል ነው የምታልፈው እኔ ያልገባኝ ነገር እንዴት ልክ ይሆናል? ብሎ የሚያስብ ነው። መሀይም ማለት ያልተማረ ሳይሆን መማር የማይፈልግ ነው። የሰይጣን ትልቁ ግዛቱ ድንቁርና ነው። ሰዎች የህሊናን አይናቸውን ካላሳወረ በቀር አያመልኩትምእና ህሊናቸውን ያጨልማል ማወቅ እንደጨረሰ ሰው የምትኖር ከሆነ መኖርህ ምክንያት አልባ መሆኑን አስብ። ባለህበት ጉድጓድ መጠን ሁሉንም ነገር ካየሀው ሁሉም ነገር ይጠብብሀል። ትንሽ እውቀትም የስጋን ሀይልን ይሻልና እውቀትህን አሟላው

    በጉልበቱ እያስፈራራ ከደጀ ሰላም የሚበላ አንድ ወጠምሻ ሰው ነበረ። የሌሊቱን ቁመት ሳይቆም ደግሞም ቅዳሴ ሳይቀድስ ያለ’ፋበትን እንጀራ በመብላቱ ቀሳውስቱ ሁል ጊዜ ቢያጉረመርሙበትም ማንም ደፍሮ የከለከለው አልነበረም። እርሱም ያልተማረ እንደሚሉት ስለሚሰማ እማራለው ብሎ ወደ አንድ መምህር ሄዶአባቴ ዳዊት አስደግሙኝብሎ ይጠይቃቸዋል። እርሳቸውምአንተ ተማር እንጂ እኔ ምን ከብዶኝ?” ብለው በደስታ እሺ ብለው ማስተማር ጀመሩ።አርሱም መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ አንድ በደንብ እንደቻለ በቃኝ አላቸው። እሳቸውም ገና እኮ ነው ቢሉትአይ አባቴ ይህቺህ ትምህርቴ ከዱላዬ ጋር ትበቃኛለችአላቸው ይባላል ዛሬም ከዱላዬ ጋር ትንሽ እውቀቴ ትበቃኛለች ብለው የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው። አንተ ግን እንደ እነርሱ አትሁን።
                            http://awdemihret.blogspot.com

ማኅበረ ቅዱሳን እና ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልእ አይተዋወቁም!

  To read in PDF ( Click Here )
                            A source from: www.abaselama.org
አክራሪውና ወግ አጥባቂው የሰለፊያ የግብር ወንድም ማኅበረ ቅዱሳን የተመሰረተበትን 20 ዓመት ሰባት ያህል ወራትን አሳልፎ ሚያዝያ 27 በእግር ጉዞ ሊያከብር መሆኑን ሲገልጽ የቆየ ቢሆንም፣ የተመዝጋቢ ቁጥር በማነሱና በሌላም ምክንያት መራዘሙ እየተወራ ነው። ይሁንና ማስታወቂያው ላይ በትልቁ የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ፎቶ ተሰቅሏል። የእርሱ የጉዞ መርሀ ግብርና አቡነ ጎርጎርዮስ፣ የእርሱ 20 ዓመትና አቡነ ጎርጎርዮስ ምን እንዳገናኛቸው ለጊዜው ባይታወቅም ብቻ ፎቷቸው በትልቁ የማስታወቂያው ማዳመቂያ ሆኗል።
1980 ብፁዕነታቸው እስካረፉበት እስከ 82 . ድረስ ወደ ዝዋይ የካህናት ማሰልጠኛ ገብተው የተማሩ አንዳንድ የዩኒቨርሲቲና የኮሌጅ ተማሪዎች መካከል አንዳንዶቹ በኋላ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን መስራቾች እንደነበሩ ይነገራል። ይህን አጋጣሚ መነሻ በማድረግ ነው ማኅበሩና የማኅበሩ ሰዎች ብፁዕነታቸውን የማኅበሩ መስራች አባት አድርገው ይቆጥራሉ።
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን በቅርብ የሚያውቋቸው እንደሚናገሩላቸው ግን ቤተ ክርስቲያን በለውጥ ጎዳና ላይ እንድትራመድ የሚፈልጉ ሰው ነበሩ። ይሁን እንጂ ከሕዝቡ ወግ አጥባቂነትና ንቃተ ህሊና አንጻር ለውጡ አዝጋሚ መሆን እንዳለበት ነበር የሚያምኑት ይባላል። ከላይ እንደገለጽኩት ይህ የብፁዕነታቸው ዓላማ ባይገባቸውም አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን ቀደምት ሰዎች ዝዋይ ከርመው ተመልሰዋል። ምክንያቱም እነዚህ የማኅበሩ ሰዎችና ማኅበሩም እንደማኅበር ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ውጪ መሆናቸውን እየታዘብን ነው። ዛሬ የማህበሩ ሰዎች በስፋት የሚቃወሙት ብፁዕነታቸው በጽሁፍ ያስተላለፏቸውን ትምህርቶች ነው። የማኅበሩ መሠረት ወንጌል ሳይሆን ተረት ነውና።

Saturday, April 28, 2012

16 ክርስቲያኖች ታሰሩ!

ታቸው ዶኒ አስቸጋሪና ለቤተክርስቲያን የማይመች ሰው መሆኑን እናውቃለን። አጥማቂ ነኝ እያለ ቅብዓ ቅዱስና እምነት ነው፤ እያለ አፈር እንደሚሸጥም ይታወቃል። በሽሮ ሜዳ ሥላሴ፣ በቃሊቲ ማርያምና በአቃቂ መድኃኔ ዓለም በሺናሻ ቅጠል ብዙዎችን ሲያጮህ የነበረ ሰው ነው። ሌላም ሌላም ነገር.....! ሰውዬው ለቤተክርስቲያን ሸክምና እንቅፋት ከመሆን ባለፈ መፍትሄ መሆን የሚችል ሰው አይደለም። ደጀ ብርሃን ብሎግም ከሰውዬው ጠባይ የተነሳ በባቦ ጋያ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አካባቢ ምስቅልቅል ከመፍጠር አይመለስም ብሎ ስለሚገምት በዓላማና በአቋም ባንመሳሰልም የቤተክርስቲያን ችግር የእኛም ችግር ስለሆነ ከአንድ አድርገን ብሎግ ላይ የወጣውን መረጃ እንዳለ አቅርበነዋል።
(አንድ አድርገን ሚያዚያ 19 ፤ 2004ዓ.ም)፡- የባቦጋያ መድሀኒአለም ቤተክርስትያን የቦታ ጉዳይ ለያዥ ለገናዥ እያስቸገረ ይገኛል ፤  ጌታቸው ዶኒ እንዳሰበው ነገሮች እየሄዱ አለመሆናቸውን ሲረዳ የቤተክርስትያኒቱን ቄሰ ገበዝ ትላንት አመሻሽ ላይ የመቅደሱን ቁልፍ ካለመጡ ብሎ ጠይቋቸው ነበር ፤ እርሳቸውም ‹‹አንተ ማነህና ነው የቤተክርስትያኒቱን ቁልፍ የምሰጥ ›› በማለት እምቢ ሲሉት ጉልበት ተጠቅሞ ቁልፉን እጁ ለማስገባት ሙከራ አድርጎ  ነበር ፤ ቄሰ ገበዙ የመቅደሱን ቁልፍ አልሰጥም በማለት ለአካባቢው ክርስትያኖች ስልክ ደውለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ክርስትያኖቹ የተሰበሰቡ ሲሆኑ ከደቂቃዎች በኋላ ጌታቸው ‹‹አመጽ ለማስነሳት ሰዎች ተሰብስበዋል›› ብሎ በደወለላቸው ፖሊሶች አማካኝነት በጊዜው የነበሩትን 16 ክርስትኖችን  እስር ቤት ሊያስገቧቸው ችለዋል ፡፡ ከእነዚህ ውስጥም ሶቶች ጎልማሶችና ፤ ወጣቶች ይገኙበታል ፤  የእነዚህ ንጹሀን ክርስትያኖች  ተቃውሞ ‹‹ጌታቸው ዶኒ  የቤተክርስትያኒቱን ቁልፍ ለምን ይቀበላል ? ቁልፉን ተቀብሎ ከዚህ በፊት ሲናገር እንደነበረው የባቦጋያን መድሀኒአለም ቤተክርስትያን ለመዝጋት የሚያደርገውን ተግባር እንቃወማለን ፤ ›› በማለታቸው ነው ለእስር የበቁት፡፡