Saturday, April 28, 2012

ደጀ ሰላም ብሎግ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት ሲል ህገ መንግሥቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የሁሉም ሃይማኖቶች ሀገር ናት ይላል! የደሴቲቱ ገዢስ ማኅበረ ቅዱሳን ይሆን?

 ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት ካልን እስላሞቹና ሌሎቹ ወደየት ይድረሱ?
ደጀ ሰላም ብሎግ- ህገ መንግሥት፣ የጠ/ሚኒስትር መግለጫ፣ ገለመሌ አይሰራም የሚል ይመስላል፤ ይህንን የሚያረጋግጠው ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት መሆኗን ከሁለት ዓመት በፊት ዘግቦ ነበር። ሌሎች ሃይማኖቶች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉና ሊኖሩ እንደሚገባ አምኖ ባለመቀበል ሀገሪቱ የአንዲት ሃይማኖት ደሴት ናት ማለት ምን ማለት ነው? ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ኢትዮጵያ የክርስቲያኖች ብቻ ናት እንደማይል ይታወቃል። እነዚህኞቹ ግን የክርስቲያን ብቻ ደሴት ነን እንዲል በመንፈሳዊ ታዛ ተጠልለው ይቀሰቅሱታል። ሰለፊ/ወሀቢ የሚባለው ደግሞ በሌላኛው ጽንፍ በኢትዮጵያ የሙስሊም መንግሥት መቆም ይገባዋል ይላል። ማሸበር የሚባለውስ ከዚህ ወዲያ ምን ሊሆን ይችላል? ይህንን የቲ-ሸርት ጫወታ የማኅበረ ቅዱሳን ሌላኛው አፍ እንደሆነ በሚነገርለት ከደጀ ሰላም ብሎግ ላይ ያገኘነው ስለሆነ ያንብቡትና ሚዛናዊ ግምትዎን ይውሰዱ።

(ደጀ ሰላም፤ ጃኑዋሪ 17/2010):- በዓለ ከተራ ሰኞ በመላ ኢትዮጵያ ታቦታተ ሕጉ ከየመንበራቸው ወጥተው ይከበራል። በሀገራችን ዋና ከተማ በአዲስ አበባ በዐቢይነት በጃን-ሜዳ ሲከበር፣ በመላው ሀገሪቱ ደግሞ ታቦታተ-ሕጉ ወደ ጥምቀተ-ባሕር ወደሚፈጸምባቸው ውሃዎች ይወርዳሉ። ከተራን ማክበር አዲስ አይደለም። ነገር ግን አምና በተከበረው “የከተራ” በዓል ላይ የታየው የሕዝቡ አከባበር፣ ሥነ ሥርዓቱና በጎ አርአያው ተጠቃሽ በመሆኑ ልናስታውሰው ወደድን። ወጣቶች አንድ ዓይነት ካናቴራ (ቲ-ሸርቶች) አሰርተው በመልበስ ራሳቸው የሕዝባቸውና የበዓላቸው አስተናባሪ ሆነው የታዩበት ሁኔታ ሁሉንም ያስደመመ ነበር። ከመንግሥት እስከ ቤተ ክህነት ባለሥልጣናት፣ ከኦርቶዶክሳውያን እስከ ሌሎች እምነት ተከታዮች ድረስ መነጋገሪያ መሆኑ ይታወሳል። በወቅቱም የሚከተሉትን መዘገባችን ይታወሳል።






የአባቶቻችንን ርስት ምን ያህል እንፈልገዋለን?
(በብርሃናዊት)

በዘንድሮው የጥምቀት በዓል ላይ: የተለያዩ ኢትዮጵያውያን "ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" እና "የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም" የሚሉ ጽሑፎች የታተሙበትን ቲሸርቶች ለብሰው በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ሳይ: ሁለት ዓይነት ስሜት ተሰማኝ::

1. የመጀመርያው ሕዝበ-ክርስቲያኑ ለእምነቱና የእምነት ሥርዓቱን በነጻነት ለማካሄዱ ምን ያህል ተቆርቋሪ እንደሆነና: ሙሉ ለሙሉ የእምነቱን ጉዳይ ችላ እንዳላለው: ምናልባትም እንደማይለውም ጭምር የተረዳሁበት ስለሆነ: አዎንታዊ ገጽታው ታይቶኛል::

2. ሁለተኛው ስሜቴ ግን: ሕዝበ-ክርቲያኑ ስሜቱ እንደሻከረና: በትንሹም በትልቁም ሊገነፍል የሚችል ስሜታዊነትን እንዲያዳብር በጽንፈኞች መደረጉን ሳይ የፈጠረኝ ስሜት ነው:: በእውነቱ መልካሙን መንፈሳዊነት የሚያደፈርስና የሚሠርቅ: የጨቅጫቃ መናፍቃንና የተንኳሽ ጽንፈኞች ፍላጻ የኢትዮጵያን ሕዝበ ክርስቲያን ወግቶ እስከዛሬ ሳይገድለው በመቅረቱ ጥበበ-እግዚአብሔርን እንዳደንቅ ተገድጃለሁ:: ሰአሊ ለነ ቅድስት የምንላት ድንግል ማርያም አሁንም በእኛ ተስፋ አልቆረጠችም::

Friday, April 27, 2012

አዲስ አበባ በሚገኙ አንዳንድ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሱቆች ላይ የማሸግ እርምጃ ተወሰደ!

ሊያደርግ ያቀደውን የእግር ጉዞ ለሌላ ጊዜ አስተላለፈ
አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሱቆች ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱን የደረሱን መረጃዎች አመለከቱ፡፡ በተለይም በኡራኤልና በሜክሲኮ አካባቢ የሚገኙ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" ሱቆች ላይ "ባልተፈቀደ የንግድ ሥራ ላይ ስለተሠማራ ሱቁ ታሽጓል" በሚል ማስታወቂያ የታሸጉት እነዚህ ሱቆች፣ "ማኅበረ ቅዱሳን" ከማንኛውም አካል የንግድ ሥራ ፈቃድ ሳይወስድ የሚሠራባቸው መደብሮች መሆናቸው ታውቋል፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" በፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ እንዲሁም በቤተክርስቲያን ስም እና በራሱ ስም እያዛነቀ ሚናው ባልለየ እንቅስቃሴ ውስጥ እዚህም እዚያም የሚነከር በመሆኑ በሰሞኑ ከሕግ ጋር ለመፋጠጥ ተገዷል ተብሏል፡፡ ከንግድ ሥራ ጋር በተያያዘም ለመንግሥትም ሆነ ለቤተክርስቲያን ተገቢውን ገቢ ሳያስገባ ዝም ብሎ የሚዘርፍ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን ሕጋዊ መሥመር እንዲይዝ ሲደረግ ጨርሶ ፈቃደኛ ሊሆን አለመቻሉ ተገልጿል፡፡

ፍትወተ - ሥጋ


- ትንሹ እሳት (የዓለም፣ የሥጋ፣ የሰይጣን እሳት)
በመሠረቱ  ማንኛውም እሳት ኃይል ነው (አለው)፡፡ በትክክል ከሠሩበት ጠቃሚ ነው፡፡ ያለ አግባብ ከሠሩበት ደግሞ አጥፊና ደምሳሽ ነው፡፡ በዘህ ክፍል ውስጥ ከሚገኙት የእሳት ዓይነቶች ውስጥ አንዳንዶቹ ምንም ጥቅም የማይገኝባቸው፣ እንዲያውም አጥፊ ብቻ የሆኑ እሳቶች ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ በአግባቡና በእግዚአብሔር ፍቃድ መሠረት ከተሠራባቸው ለበረከት የሚሆኑ፣ በሥጋ ምሪት ከተሠራባቸው ደግሞ የኩነኔ መሰላሎች የሆኑ እሳቶች ናቸው፡፡
1. ፍትወተ - ሥጋ (Sex) - እግዚአብሔር ለሰዎች ከሰጣቸው ጠቃሚ ኃይሎች አንዱ የሆነው ፍትወተ ሥጋን በአብዛኛው ለክፋት መገልገያነት ሲውል ማየታችን መጥፎ እንደሆነ አድርገን እንድንመለከተው አድርጎናል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመርኩዘን ስለዚህ ጉዳይ ያጠናን እንደሆነ ግን መልካም ስጦታ እንደሆነ ነው የምናገኘው፡፡ ይህን ስጦታ በአግባቡ ለተጠቀመበት ሰው የበረከት ምክንያት ይሆንለታል፡፡ ከጌታ ፍቃድ ውጪ ለሠራበት ደግሞ የጥፋት መሣሪያ ይሆንበታል፡፡ "እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፣ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡፡ እግዚአብሔርም ባረካቸው፣ እንዲህም አላቸው፡- ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት...." (ዘፍ. 127-28) ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያው ገጽ ጥቅስ አንስቶ በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ጋብቻና የጋብቻ ውጤቶች የሆኑት ልጆች የእግዚአብሔርን ቡራኬ ሲቀበሉ እናያለን፡፡ በጋብቻ ውስጥ ውትወተ ሥጋ አለ፣ ቀጥሎም ልጆች ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ በቃል ኪዳን መሐላ ማኅተም በታሰረ ጋብቻ ውስጥ የባልና ሚስት ግንኙነት የተቀደሰ ተግባር እንጂ፣ ርክሰት አይደለም፡፡ በዚህ መልኩ ብቻ ከተሠራበት የፍትወተ-ሥጋ እሳት ጠቃሚና ቅዱስም ይሆናል፡፡ ከዚህ ውጪ ግን የገሃነመ እሳትን የመጀመሪያ ነበልባሎች እዚህ ምድር ላይ የሚጭር እርኩስ እሳት ይሆናል፡፡ ፍትወተ-ሥጋ እሳት ስለመሆኑ ቅዱስ ጳውሎስ በተለያዩ መልእክቶቹ አመልክቷል፡፡ ለምሳሌ 1 ቆሮ. 78-9 ላይ እንዲህ ይላል - "ላላገቡና እንዲሁም ባሎቻቸው ለሞቱባቸው ሴቶች የምለው እንዲህ ነው፤ ሳያገቡ እንደ እኔ ቢኖሩ መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ራሳቸውን መቈጣጠር ቢያቅታቸው ያግቡ፤ ምክንያቱም በሥጋ ምኞት ከመቃጠል ይልቅ ማግባት የተሻለ ነው፡፡" የሥጋ ምኞት (ፍትወት) ለምን ያቃጥላል; መልሱ ግልጽ ነው እሳት ስለሆነ፡፡ እዚህ ላይ .ጳውሎስ ስለዚህ እሳት መልካምነት ይናገራል፡፡ በሌላ ቦታ ግን ያለአግባቡ በጥቅም ላይ ስለዋለ ርኩስ እሳት ይናገራል፡፡