ሊያደርግ ያቀደውን የእግር
ጉዞ ለሌላ ጊዜ አስተላለፈ
አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙ የ"ማኅበረ ቅዱሳን"
ሱቆች ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱን የደረሱን መረጃዎች አመለከቱ፡፡ በተለይም በኡራኤልና በሜክሲኮ አካባቢ የሚገኙ የ"ማኅበረ
ቅዱሳን" ሱቆች ላይ "ባልተፈቀደ የንግድ ሥራ ላይ ስለተሠማራ ሱቁ ታሽጓል" በሚል ማስታወቂያ የታሸጉት
እነዚህ ሱቆች፣ "ማኅበረ ቅዱሳን" ከማንኛውም አካል የንግድ ሥራ ፈቃድ ሳይወስድ የሚሠራባቸው መደብሮች መሆናቸው
ታውቋል፡፡
"ማኅበረ ቅዱሳን" በፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ እንዲሁም
በቤተክርስቲያን ስም እና በራሱ ስም እያዛነቀ ሚናው ባልለየ እንቅስቃሴ ውስጥ እዚህም እዚያም የሚነከር በመሆኑ በሰሞኑ ከሕግ ጋር
ለመፋጠጥ ተገዷል ተብሏል፡፡ ከንግድ ሥራ ጋር በተያያዘም ለመንግሥትም ሆነ ለቤተክርስቲያን ተገቢውን ገቢ ሳያስገባ ዝም ብሎ የሚዘርፍ
ድርጅት እንደመሆኑ መጠን ሕጋዊ መሥመር እንዲይዝ ሲደረግ ጨርሶ ፈቃደኛ ሊሆን አለመቻሉ ተገልጿል፡፡