(ከደጀ ብርሃን) ጅምሩ ጥሩ ነበር። የሰበሰባችሁትን የቤተክርስቲያን ገንዘብ ከማስወረሳችሁ በፊት ወይም ስትነግዱብን ኖራችሁ የሚሉትን ድምጾች ለማፈንና ይህንን የመሰለ ትሩፋት እየሰራን ነው ለማለት ያደረጋችሁት ይመስላል። ባካፋ ዝቃችሁ እጣንና ጧፍ ከመበተን ያለፈ ቋሚ ስራ ስትሰሩ አልነበራችሁም። ይሁን እንጂ ገንዘባችንን ከቀበራችሁበት ስላወጣችሁና ምንም ይሁን ምንም እንጥፍጣፊው ስለደረሰን አመስግነናል።
በእንዳለ ደምስስ
ማኅበረ
ቅዱሳን በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኘውን የደብረ ኀይል ወደብረ ጥበባት በዓታ ለማርያም የአቋቋም ምስክር
ትምህርት ቤትን በ4.6 ሚሊዮን ብር ለመገንባት ሚያዚያ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. የግንባታ ውል ስምምነት ከአስማማው
አያሌው ሕንጻ ሥራ ተቋራጭ ጋር ተፈራረመ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ልማት ዋና ክፍል አስተባባሪነት
የሚከናወነው ይኸው ፕሮጀክት ማኅበረ ቅዱሳንን በመወከል የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኀ/ማርያምና የሕንፃ ሥራ
ተቋራጩ ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ አስማማው አያሌው አማካይነት የፊርማ መርሐ ግብሩ ተፈጽሟል፡፡
በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጽ/ቤት በተከናወነው የፊርማ መርሐ ግብር
ላይ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኀ/ማርያም ባደረጉት ንግግር ‹‹ 4.6 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ፕሮጀክት ቀርጾ
የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤት ለመገንባት ከዚህ በፊት አድርገነው አናውቅም፡፡ ይህ ትልቅ እድገት ነው፡፡
ምእመናንም ማኅበረ ቅዱሳንን ማመን የቻሉበት ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ ማኅበረ ቅዱሳን ይሥራው
ለማለት መቻል ሙሉ ለሙሉ በማኅበሩ ላይ እምነት እንዳሳደሩ ነው የሚያሳየው፡፡ እኛም በታማኝነት ትኩረት ሰጥተን
እንድንሠራ የሚያደርገን ነው፡፡ ጨረታውን ከብዙዎቹ የሕንጻ ሥራ ተቋራጮች ጋር ተወዳድሮ ያሸነፈው ድርጅት በማኅበሩ
ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገና አብሮ የኖረ ነው፡፡ ሥራውንም በጥራትና ከተያዘለት ጊዜ ቀደም ብሎ በማጠናቀቅ
ያስረክባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን በኩልም ሥራውን ለማፋጠን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ
አረጋግጣለሁ›› በማለት ገልጸዋል፡፡