(ከደጀ ብርሃን) ጅምሩ ጥሩ ነበር። የሰበሰባችሁትን የቤተክርስቲያን ገንዘብ ከማስወረሳችሁ በፊት ወይም ስትነግዱብን ኖራችሁ የሚሉትን ድምጾች ለማፈንና ይህንን የመሰለ ትሩፋት እየሰራን ነው ለማለት ያደረጋችሁት ይመስላል። ባካፋ ዝቃችሁ እጣንና ጧፍ ከመበተን ያለፈ ቋሚ ስራ ስትሰሩ አልነበራችሁም። ይሁን እንጂ ገንዘባችንን ከቀበራችሁበት ስላወጣችሁና ምንም ይሁን ምንም እንጥፍጣፊው ስለደረሰን አመስግነናል።
በእንዳለ ደምስስ

በማኅበረ ቅዱሳን ዋና ጽ/ቤት በተከናወነው የፊርማ መርሐ ግብር
ላይ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ዲ/ን ሙሉጌታ ኀ/ማርያም ባደረጉት ንግግር ‹‹ 4.6 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ፕሮጀክት ቀርጾ
የአቋቋም ምስክር ትምህርት ቤት ለመገንባት ከዚህ በፊት አድርገነው አናውቅም፡፡ ይህ ትልቅ እድገት ነው፡፡
ምእመናንም ማኅበረ ቅዱሳንን ማመን የቻሉበት ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አውጥቶ ማኅበረ ቅዱሳን ይሥራው
ለማለት መቻል ሙሉ ለሙሉ በማኅበሩ ላይ እምነት እንዳሳደሩ ነው የሚያሳየው፡፡ እኛም በታማኝነት ትኩረት ሰጥተን
እንድንሠራ የሚያደርገን ነው፡፡ ጨረታውን ከብዙዎቹ የሕንጻ ሥራ ተቋራጮች ጋር ተወዳድሮ ያሸነፈው ድርጅት በማኅበሩ
ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገና አብሮ የኖረ ነው፡፡ ሥራውንም በጥራትና ከተያዘለት ጊዜ ቀደም ብሎ በማጠናቀቅ
ያስረክባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን በኩልም ሥራውን ለማፋጠን አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ
አረጋግጣለሁ›› በማለት ገልጸዋል፡፡