Friday, April 20, 2012

ምን አለበት?

አዳምና ሔዋን

***********

አንተ አዳም ራስ ነህ

ብሏል ቅዱስ ቃሉ፤

አንቺ ሔዋን አንገት ነሽ

ብለው ያወራሉ

እንግዲህ ተስማሙ

አንተ ራስ፤

እርሷ አንገት፤

ብታሽከረክርህ …..

ታዲያስ ምን አለበት?
**********
ከደረጀ በላይነህ

Thursday, April 19, 2012

ማህበረ ቅዱሳንና ሰለፊያ!! ግልባጩ ማነው?

                                                                                              source:awdemihret.blogspot.com
የማህበረ ቅዱሳን ሰለባ የሆኑ ብዙ የቤተክርስቲያን አባቶችና ልጆች ማቅን በአሸባሪነት ከፈረጁት ዓመታት የተቆጠሩ ቢሆንም፣ ማቅ ግን እንዲህ የሚሉኝ ለቤተ ክርስቲያን ጥብቅና ስለቆምኩ ነው በሚል ራሱን ሲከላከል ቆይቷል። ማህበሩ አሸባሪ የመሆኑ ጉዳይም በአንዳንዶች ዘንድ እንደ ስድበ ሲቆጠር መቆየቱ ይታወሳል። ለማኅበሩ ይህ ስም የተሰጠው በከንቱ አልነበረም። ስራው በአክራሪ ሙስሊሞች ከሚካሄደው የበለጠ እንጂ ያላነሰ ሆኖ ስለተገኘ ነበር ይህ የግብር ስም የወጣለት።

 ዕድሜ የሰጠው ሰው ብዙ ያያልና ይኸው የማህበሩ የግብር ስም ከትናንት በስቲያ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ጸድቋል። በማኅበሩ ሲገፉና ሲነቀፉ ለኖሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ይህ እንደ አንድ ትልቅ ድል የሚቆጠር ነው። እንኳንም በትክክል የወጣለት የግብር ስም በማኅበሩ ዘንድ እንደ ስድብ ከመቆጠር አልፎ ትክክለኛ የማህበረ ቅዱሳንን ማንነት የሚገልጥ ስም ሆኖ ተነገረ! ይህን የተናገሩት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትራችን መሆናቸው ትልቅ ግምት የሚሰጠው ብቻ ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያንን ከማሸበር አልፎ አገርንም ለማተራመስ ትልቅ አላማ እንዳለው በመንግስት በኩል የተደረሰበት መሆኑን ያመለክታል።   

በአሁኑ ጊዜ ማኅበረ ቅዱሳን ማነው? ምንስ ነው የሚሰራው? አላማው ምንድነው ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች ምላሽ የሚፈልገው የህብረተሰብ ቁጥር እየበዛ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ  ሰለፊያን አስመለክተው ሲናገሩ ሰለፊያ የማኅበረ ቅዱሳን ግልባጭ መሆኑን በግልጽ ቋንቋ እንዲህ ሲሉ ነግረውናል። “አንዳንድ የሰለፊ እምነት ተከታዮች አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት የሚያራምዱትን ግልባጭ ሲያራምዱ ይታያሉ።” ማኅበረ ቅዱሳን ለክፋት መምህር እንጂ ደቀመዝሙር እንደማይሆን የተረዱት ጠቅላይ ሚኒስትር ማኅበረ ቅዱሳን ስልቶቹንና አካሄዱን ለሰለፊያ ማውረሱን በማያሻማ መንገድ ገልጸዋል፡፡
መቼም ማቅ የሚሰራውን ስራ አስተውሎ ያየ ሰው በማቅና በሰለፊያ(ወሀቢያ) መካካል ያለውን የመንፈስ አንድነት በቀላሉ ይረዳል። ለማስረጃ ያህል፡-

«አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት»ማለት ምን ማለት ነው?

በአንድ ወቅት መጠሪያ ስሙ «ማሞ» የሚባል ሰው የፍተሻ ኬላ ላይ ጠባቂ ያስቆመውና የይለፍ ወረቀት እንዲያሳይ ይጠይቀዋል። አቶ ማሞም በፎቶግራፍ የተደገፈ ማንነቱን ገላጭ መታወቂያ ከኪሱ መዘዝ ያደርግና ለኬላ ጠባቂው ያሳያል። ኬላ ጠባቂውም በአካለ ሥጋ ከፊቱ የቆመውን አቶ ማሞንና የመታወቂያው ላይ የማሞን ፎቶ ቢያስተያይ ጨርሶውኑ የሚመሳሰሉ አልሆን ይለዋል።
 ኬላ ጠባቂ ቢቸግረው ጊዜ ስማ ሰውዬው ስምህ ማነው? ብሎ ይጠይቀዋል።
አቶ ማሞም « ማሞ» እባላለሁ በማለት መልስ ይሰጣል።
 ኬላ ጠባቂውም እንደገና- ይኼ መታወቂያ እኮ ማሞ የሚል ስም የለውም! ይለዋል።
አቶ ማሞም አዎ ልክ ነው። «ማሞ» የሚል ስም የለውም ይላል እያረጋገጠ።
አንተ ማሞ የምትባል ከሆነ ማሞነትህን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ማሳየት ሲገባህ ለምን ማሞ ያልሆነ መታወቂያ ታሳየኛለህ? ይላል ኬላ ጠባቂው በንዴት።
እውነተኛው ማሞም ስለማንነቱና እውነተኛ ስላልሆነው የማሞ መታወቂያ ማስረዳት ጀመረ።
እኔን ለማወቅ የፈለጉ ኬላ ጠባቂዎች  የምላቸውን እንዲሰሙኝ እኔ እስከነ ሕይወቴ ቆሜ ለማስረዳትና፣ መታወቂያ ማየት ሲያምራቸው ደግሞ ይህንን የኔን ማንነት የማይገልጸውን የወንድሜን መታወቂያ ይዣለሁ ብሎ እብደት ቀመስ ማብራሪያውን አቀረበ።
ያኔም ኬላ ጠባቂው እንደእብድ ሳይሆን ሆን ብሎ እንደሚያምታታ ገብቶት፣ «ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ» ብሎ ሲያበቃ ሰውዬው ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ ባለመያዙና የራሱ ያልሆነ መታወቂያ አላግባብ ይዞ በመገኘት ወንጀል እንዲጠየቅ ወደማረፊያ እንዲሄድ የመደረጉን ታሪካዊ ወግ ከዓመታት በፊት አዳምጠናል።
ይህንን ገላጭ ወግ እዚህ ላይ ያነሳነው ያለምክንያት አይደለም። በትናንትናው ምሽት የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስለ «ኢስላማዊው ሰለፊና ስለኦርቶዶክሱ ማቅ ሰለፊ» ማንነት  የተነተኑበት የመንግሥታቸውን አቋም ተንተርሶ «አንድ አድርገን» ብሎግ ምሬቱን ሲገልጽ አግኝተነዋል።