መድኅነ ዓለም ክርስቶስ የአዳምን ልጆች በደልና የሕግ እርግማን ተሸክሞ ቀራንዮ ላይ መሰቀሉን እናውቃለን።
የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ኢየሱስ ቤዛ ይሆን ዘንድ ያስገደደው ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር ብቻ ነው። ይህንንም አባ
ሕርያቆስ በቅዳሴው «ፍቅር ሰሀቦ ለወልድ ኃያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት» ሲል ለእኛ ያለውን ጥልቅ ፍቅር
ገልጾታል። ከዚህ ውጪ ሌላ ዓላማ አልነበረውም።
ሮሜ ፭፣፰
እንግዲህ ይህ ፍቅር ለእኛ የተደረገው እኛ ደጎች ስለነበርን ሳይሆን የእኛ በደል ከፍቅሩ ውጪ ስላወጣን ዳግም በማያልቀው ፍቅሩ ውስጥ እንድንኖርለት ስለፈለገ ብቻ ነው። ወሰን በሌለው ፍቅሩ ውስጥ እንድንኖርለት አርአያውና ፍለጋውን ሁሉ ሰርቶ አሳይቶናልና የሕይወታችን አንድ አካል እንዲሆንለት ይሻል። ለእኛ የተሰጠው አምላካዊ ፍቅር በእኛ ውስጥ መኖር ይገባዋል። እኛ ኃጢአተኞች ሳለን ከተወደድን ልንጠላው የሚገባው የሰው ልጅ የለም ማለት ነው።
በክርስቶስ ደም የተመሠረተው ወንጌል እኛን ጠላቶቹ ሳለን ወደ ፍቅሩ መመለስን ብቻ ሳይሆን «ጠላትህን ጥላ» የሚለውንም የጥል ሕግ አፍርሶ «ጠላትህን ውደድ» የሚልም ትእዛዝ ትቶልናልና ነው።
«ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል» ሮሜ ፭፣፰
እንግዲህ ይህ ፍቅር ለእኛ የተደረገው እኛ ደጎች ስለነበርን ሳይሆን የእኛ በደል ከፍቅሩ ውጪ ስላወጣን ዳግም በማያልቀው ፍቅሩ ውስጥ እንድንኖርለት ስለፈለገ ብቻ ነው። ወሰን በሌለው ፍቅሩ ውስጥ እንድንኖርለት አርአያውና ፍለጋውን ሁሉ ሰርቶ አሳይቶናልና የሕይወታችን አንድ አካል እንዲሆንለት ይሻል። ለእኛ የተሰጠው አምላካዊ ፍቅር በእኛ ውስጥ መኖር ይገባዋል። እኛ ኃጢአተኞች ሳለን ከተወደድን ልንጠላው የሚገባው የሰው ልጅ የለም ማለት ነው።
በክርስቶስ ደም የተመሠረተው ወንጌል እኛን ጠላቶቹ ሳለን ወደ ፍቅሩ መመለስን ብቻ ሳይሆን «ጠላትህን ጥላ» የሚለውንም የጥል ሕግ አፍርሶ «ጠላትህን ውደድ» የሚልም ትእዛዝ ትቶልናልና ነው።
« ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና» ሮሜ ፭፣፵፫-፵፭
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና» ሮሜ ፭፣፵፫-፵፭
የሰማዩ
አባታችን ልጆች እንሆን ዘንድ ለእኛ ለተጠላነው ጥልቅ ፍቅሩን በልጁ ሞት ስላሳየ እኛም እንዲሁ
በፍቅሩ የልጅነት ሕይወት ውስጥ ለመቆየት የግድ ጠላቶቻችንን መውደድ፣ የሚረግሙንን መመረቅ፣ ለሚጠሉን መልካም
እንድናደርግ ይፈልጋል። ከጥላቻና ከእርግማን ጎራ ወደ ፍቅርና በጎነት መንፈሳዊ ዓለም እንድንገባ ያዘናል።
ያለበለዚያማ ልጆቹ ልንሆን እንዴት ይቻላል? ፍቅርና እርግማን መቼም ቢሆን ስምምነት ይኖራቸው ዘንድ አይታሰብም። ስለዚህም የፍቅር አባት ልጆች ረጋሚዎችና ጥላቻን የተሞሉ ሊሆኑ በፍጹም አይችሉም።
በእርግጥ በአፋችን የሰማዩ አባታችን ልጆች ስለመሆናችን እንናገር ይሆናል። ልዩነቱን ግን በእኛ ላይ የሚገልጠው ልጅነታችንን ስላወራን ሳይሆን የሚመሰክርብን ፍቅር የራቀው ማንነታችን ነው። ቃሉን የሚያወሩ እንጂ የማያደርጉ ስለሆንን ስንት የእርቅ በሮችን ዘግተን በጥላቻና በእርግማን ዓለም ውስጥ ዛሬም ድረስ አለን።