(BY DEJEBIRHAN)
በእውነት፣ እውነተኛ ሰባኪ ማነው? ምን ይመስላል? ምንስ መምሰል አለበት? በዚህ ዘመን ምላሽ የሚያስፈልገውና በቂ መልስም ያልተገኘለት አገልግሎት ቢኖር ይህ «ሰባኪ» የሚባለው የግብር ማንነትን የሚገልጸው ቃል ነው። መልሱ ያልተገኘው፣ መልስ ስለሌለው ሳይሆን መልስ የሚያስፈልገው የሰባኪነት ሕይወት በዘመናችን ከመጥፋቱ የተነሳ ነው። ዳዊት ሁሉም የስህተት መንገድ ሂያጆችን በሚኖሩበት ውድቀት ውስጥ « ኵሉ ዐረየ፣ ወኅቡረ ዐለወ» ሲል ያስቀምጠዋል። መዝ ፲፬፣፲፫
የሰባኪነት አገልግሎትና ሕይወቱን በተመለከተ ከታች በጥቂቱ እንመለከታለን።
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው «ሰባኪ»የሚለውን ቃል እንዲህ ይፈቱታል።
ወንጌላችንም በተረዳነው እውነት ሰባኪ ማለት እንዲህ ዓይነት ነው ይለናል።
«ነገር ግን ምን ይላል? በአፍህ በልብህም ሆኖ ቃሉ ቀርቦልሃል፤ ይህም የምንሰብከው የእምነት ቃል ነው»
ሮሜ ፲፣፰
የሚሰብክ የሚሰብከውን ያመነ ካልሆነ የሚሰብከውን ሰው እንዴት ማሳመንና በሚያምነው እውነት እንዲኖር ማድረግ ይችላል? ሰባኪ የሚሰብከውን ያመነና የሚያወራው ብቻ ሳይሆን የሚሰብከውን እምነት የወንጌል አደራ ራሱ የሚጠብቀው ካልሆነ እንዴት ሕይወትን በሰዎች ውስጥ መዝራት ይችላል? ሐዋርያው ጳውሎስ ለቲቶ በአንድ ወቅት እንደገለጸው ስብከት ለሰባኪው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መቀበልና ይህንንም የመቀበል አደራ በተገለጠለት ቃሉ መሠረት የመጠበቅ ግዴታ መሆኑን አስረግጦ በመናገርና በዚህም አደራው በጳውሎስ ስብከት የተነሳ ቲቶ ሃይማኖት ልጁ ለመሆን መብቃቱን እናነባለን።
ከዚህ ቃል የምንረዳው ሰባኪ የሚሰብከው እግዚአብሔር እንዳዘዘውና ስብከቱም በተሰጠው የስብከት አገልግሎት ውስጥ የእግዚአብሔር ቃል አደራውን በመግለጥ ሌሎች ወደ እውነተኛ የሃይማኖት ኅብረት እንዲመጡ ማስቻል መሆኑን ነው።
ሰባኪ የታዘዘውን ቃል በተሰጠው አደራ መሠረት ለሌሎች ማድረስ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የሚያዩለት የሰባኪነት አገልግሎት ሕይወትም በኑሮው ሁሉ ሊታይ የግድ ነው። ጳውሎስ ይህንን ነገር በራሱ ላይ የሰባኪነት አገልግሎት ምስክሮቹ በስብከቱ ቃል ወደ እምነት ኅብረት የመጡ ምእመናንና ምእመናት ስለመሆናቸው እንዲህ ሲል ያስረዳናል።

«በዘመኑም ጊዜ፥ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ፤ |
በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን» |