Thursday, April 5, 2012

ጌታ ኢየሱስ የመገበው ስንት ሰው ነው? 4ሺ ወይስ 5ሺ ሰዎችን?

የማቴዎስ ወንጌል
14፥21
ከሴቶችና ከልጆችም በቀር የበሉት አምስት ሺህ ወንዶች ያህሉ ነበር።
የማቴ ወንጌል 15፥38
የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ።
በማርቆስ ወንጌል ላይም እንደዚህ የሚል ተጠቅሷል።

የማርቆስ ወንጌል
6፥44
እንጀራውንም የበሉት ወንዶቹ አምስት ሺህ ነበሩ።
8፥9
የበሉትም አራት ሺህ ያህል ነበሩ።
8፥19
አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት መሶብ አነሣችሁ? እርሱም፦ አሥራ ሁለት አሉት።
8፥20
ሰባቱን እንጀራስ ለአራት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት ቅርጫት አነሣችሁ? እርሱም፦ ሰባት አሉት።
ታዲያ የተመገቡት ትክክለኛው የሰዎች ቁጥርና የተነሳው የቁርስራሽ ቁጥር ስንት ነው? ወንጌላውያኑስ ለምን ቁጥሮቹን አበላልጠው ዘገቡ? አልገባኝምና መልስ እሻለሁ
መልስ
(ከደጀብርሃን)
ጥቅሶቹን አበዛሃቸው እንጂ ጥያቄህ በማቴ 14፤21 እና በማቴ 15፣38 ላይ የተመገቡት ሰዎች ቁጥርና የተነሳው ቁርስራሽ መጠን የተለያየው ለምንድነው? የሚል ይመስለኛል።
ከዚህ አንጻር በአጭሩ ስመልስልህ አዎ፤ 4 ሺህ ሰዎችና 5 ሺህ ሰዎች መግቦ አንዴ 7 ቅርጫት፣ አንድ ጊዜ ደግሞ 12 ቅርጫት አትረፍርፏል። ይህንንም በአጭሩ ላብራራ።
1/ በማቴ 14፣20-21 ላይ የተመለከተው 5 ሺህ ሰዎችና 12 ቅርጫት ቁርስራሽን በተመለከተ፣
ነገሩን ለመረዳት እንድንችል ከማቴዎስ ምእራፍ 13 እንጀምር። ማቴዎስ 13 የምሳሌዎች ምዕራፍ ተብሎ በነገረ መለኰት ምሁራን ይጠራል። ምክንያቱም የዘሪው ምሳሌ ማቴ 13፣3 ፣ የሰናፍጭ ምሳሌ ማቴ 13፣31 የእንቁ ምሳሌ ማቴ 13፣44፤ የመረብ ምሳሌ ማቴ 13፣47 ፤ የተነገረበት ምዕራፍ ነው። እዚህ ላይ የምሳሌዎችን ምዕራፍ ማንሳት ያስፈለገበት ምክንያት ምሳሌዎችን ለመተንተን ሳይሆን ምሳሌዎቹ የተነገረበት ቦታና ሁኔታ በነገረ ጭብጥነት እንድንይዝ በማስፈለጉ ነው። በዚሁ መሰረት ይህ የምሳሌ ምዕራፍ ታሪክ በኢየሱስ የተነገረው ከቤቱ ወጥቶ በባህር ዳሩ አጠገብ መሆኑን ነው።
«በዚያን ቀን ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ በባሕር አጠገብ ተቀመጠ፤እርሱም በታንኳ ገብቶ እስኪቀመጥ ድረስ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፥ ሕዝቡም ሁሉ በወደቡ ቆመው ነበር» ማቴ 13፣1-2
ይህም ከቤቱ ሲል ከናዝሬት (ሉቃ 4፣16) ሲሆን የባህሩ ዳር ደግሞ ገሊላ (ማር 1፣16) መሆኑን ጥቅሶቹ ያረጋግጡልናል። ያም ማለት ከናዝሬት ወደ ገሊላ ሄዶ «የምሳሌዎቹን ታሪክ» ከባህሩ ዳር አስተማረ ማለት ነው። ከዚያስ በኋላ ወደየት ሄደ? የሚለውን ስንከተል ደግሞ ይህንን እናገኛለን። ማቴ 13፣53 ላይ ተቀምጦልናል።


Wednesday, April 4, 2012

የባቢሎን ግንብ

በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 11 ዘንድ፣ የባቢሎን ግንብ ሰማይን እንዲደርሱ የተባበሩት ሰው ልጆች የሠሩ ግንብ ነበር። ያ ዕቅድ እንዳይከናወንላቸው ለመከልከል፣ እግዚአብሔር እያንዳንዱ በተለየ ቋንቋ እንዲናገርበት ልሳናታቸውን አደባለቀ። መግባባት አልተቻላቸውምና ስራው ቆመ። ከዚያ በኋላ፣ ሕዝቦቹ ወደ ልዩ ልዩ መሬት ክፍሎች ሄዱ። ይህ ታሪክ ብዙ የተለያዩ ዘሮችና ቋንቋዎች መኖሩን ለመግለጽ እንደሚጠቅም ይታስባል።

የባቢሎን ግንብ (ዘፍ. 11፡1-9)

       ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች። ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ። እርስ በርሳቸውም፦ ኑ፣ ጡብ እንሥራ፣ በእሳትም እንተኲሰው ተባባሉ። ጡቡም እንደ ድንጋይ ሆነላቸው፤ የምድርም ዝፍት እንደ ጭቃ ሆነችላቸው። እንዲህም፦ ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስማችንን እናስጠራው አሉ። እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ። እግዚአብሔርም አለ፡ - እነሆ፣ እነርሱ አንድ ወገን ናቸው፣ ለሁሉም አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም። ኑ፣ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው። እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ። ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፣ እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል።
በትንተና
የሰው ልጆች ሁሉ አንድ ኅብረተሰብ ሆነው የሠፈሩባት አገር ሰናዖር ለኤፍራጥስ ወንዝ ቅርብ ነበረች። ባቢሎን በጥንታዊ አሦር ቋንቋ ምንጭ በተገኘ ባቢሉ (ባብ-ኢሉ) ማለት «የአማልክት በር» ለማለት ነው። በዕብራይስጥ ትርጉም ግን የ«ባቤል» ስም «መደባለቅ» ለማለት ለሚለው ቃል ይመስላል። ከውድቀቱ በፊት የተናገረው ቋንቋ አንዳንዴ «የአዳም ቋንቋ» መሆኑ ይባላል። በታሪክ አንዳንድ ሰው በግምት ያም ሆነ ይህ ቋንቋ መጀመርያው ቋንቋ እንደ ነበር የሚለው ክርክር አቅርቧል። ለምሳሌ ቋንቋው ዕብራይስጥ ወይም ባስክ እንደ ነበር ተብልዋል።
በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 10 ባቢሎን ከተማ የናምሩድ ግዛት መጀመርያ እንደ ነበር ይላል።

እኛ ጦጣ ነን?

የኛ አርኪዮሎጂስቶች ‹‹ጦጣ›› ከሚፈልጉ…

naodlive@gmail.com


አርኪዮሎጂስቶች ተግተው የሚፈልጉት ነገር ቢኖር ቅሪተ አጽም ነው፡፡ ከቻሉ የሰው ለማግኘት ይሞክራሉ፤ ካልሆነላቸው የእንስሳ አጽም፤ ካጡ ደግሞ የዕጽዋት ቅሪት፤ በጣም ከተቸገሩ ደግሞ የጥንት ሰው መገልገያ ሊሆኑ ይችላሉ ያሏቸውን ስለታም ድንጋዮችና ሸክላዎች ይፈልጋሉ፡፡
የብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን አርኪዬሎጂስቶች ሕልም ግን ሉሲን የሚቀድም የጦጣ አጽም ማግኘት ነው፡፡ ሉሲን ያገኛትም ፈረንጅ ስለሆነ ደስተኛ አይደሉም ስለዚህ የ‹‹ሀበሻን ጦጣ›› ራሱ ሀበሻ እንዲያገኝ ይፈልጋሉ፡፡ በቅርቡ ሀበሻ ተመራማሪዎች ያገኙት ቅሪተ አጽምም የተሞገሰውም የሉሲን የዕድሜ ሪከርድ ስለሰበረ እና …ነው፡፡

ይሄ ሁሉ ልፋት ግን አንድ ነገር ለማረጋገጥ ነው? እኛ ሰዎች ከጦጣ መምጣታችንን!
ሰው ከጦጣ ሊመጣ አይችልም ብዬ ለመሞገት አልፈልግም፡፡ ምን አገባኝ! የሚያምን ይመን፤ የማያምንም አለማመኑን  ይመን፡፡ እኔን የሚያሳስበኝ! ጦጣ ስንፈልግ እንደ ጦጣ ማሰብ የመጀመራችን ነገር ነው?
ያ ጦጣ፤ የመጀመሪያው ጦጣ፤ ኢትዮጵያ ብቻ መገኘቱ ነገር ለምን ጥሩ ዜና እንደሚሆን ግን አይገባኝም!፡፡ ለምን አሜሪካ አይገኝም? ለምን ዩሮፕ አይገኝም? …..አረ… ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ምንጭ ስለሆነች ነው! አይደል?፡፡ የሰው ልጅ ምንጭ ጦጣ ከሆነ፤ ያ ጦጣም ኢትዮጵያ ብቻ ከተገኘ…ኢትዮጵያውያን ከሌላው የሰው ዘር ሁሉ ተለይተን ለጦጣ የቀረብን መሆናችን አይደል? እና ይሄ ምን ያኮራል? ያሳፍራል እንጂ፡፡ እንኳንም ዘንቦብን ...