በሲዳማ፣
ጌዴኦ፣ አማሮና ቡርጂ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት በተለይም በሀዋሳ ለአንድ ዓመት ከስምንት ወራት ያህል
የቆየው ውዝግብ እስካሁን መቋጫ አለማግኘቱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ለውዝግቡ መባባስ የአቡነ ገብርኤል አንዱን
አቅርቦ አንዱን የማራቅ አድሏዊ አመራር ትልቁን ድርሻ ሲወስድ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤትና
ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ተገቢውን እርምጃ ባለመውሰዳቸው የምዕመናኑ ሰቆቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን
ከተለያዩ ምንጮች ለመረዳት ችለናል፡፡
አቡነ
ገብርኤል በሁለንተናዊ የስብዕና ቀውስ ውስጥ ያሉ ሰው ናቸው ያሉ ታዛቢዎቻችን እንዳስረዱን፣ ሊቀጳጳሱ
የሚናገሯቸውና የሚፈጽሟቸው ድርጊቶች የትላንቱ ከዛሬው፣ የዛሬው ከነገ የማይጣጣሙ ርስ በርሳቸው የሚምታቱ ናቸው
ብለዋል፡፡ በተከበረውና በተቀደሰው ዐውደ ምሕረት ላይ አንድ ጊዜ በድያለሁ ይቅርታ ሲሉ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በግል
መጽሔት ጭምር በአምሳለ ሥላሴ የተፈጠሩትን ምዕመናንንና ምዕመናትን ቀበሮዎች እያሉ የሚሳደቡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ሰውየው በዚህ ብቻ ሳያበቁ በቅዱስ ሲኖዶስ ፊት ከቤተክርስቲያን የተለየ እና የተከፈለ ሕዝብ የለም ጥቂት
ተሃድሶአውያን ናቸው እያሉ የ"ማኅበረ ቅዱሳን"ን የውሸት አሉባልታ ያስተጋባሉ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ አዎን የተሰደደ ሕዝብ አለ፡፡ ዕድሉ ይሰጠኝና ሁለቱንም አስማማለሁ እያሉ ሲማጸኑ ይታያሉ፡፡
አቡነ ገብርኤል በግል ቀርቦ ለሚያነጋግራቸው አሁን ያለው የቤተክርስቲያን ቀውስ በዋነኛነት በ"ማኅበረ ቅዱሳን" የተንኮልና
የጥፋት ዕቅድ እንደሚመራ፣ እንዲሁም አገልጋዮች ያለ ጥፋታቸው እንደሚሰደቡና በግላቸውም አገልጋዮቹን
እንደሚያደንቋቸው ሲመሰክሩ፣ በአደባባይ ሲሆን ግን ከማኅበሩ ብሰው ሽንጣቸውን ገትረው ይራገማሉ፡፡ አቡነ ገብርኤል
የማስመሰል ድርጊታቸው ከውስጥ ባህርያቸው የሚመነጭ ነው ያሉ እነዚህ ወገኖች፣ እንደማሳያ የሚሆነን በዕድሜ ያረጁ
ሆነው ሳለ ወጣት ለመምሰል ጥቁር ሂና (የፀጉር ቀለም) መቀባታቸው ራሳቸውን በወጣትነት ውስጥ ደብቀው ከሁኔታዎች
ጋር ለመመሳሰል መሞከራቸው ነው ብለዋል፡፡ ቤተክርስቲያንንም የሚያጠቁት የዋህና ምንም የማያውቅ ቅን ክርስቲያን
በመምሰል ነው ብለዋል፡፡