Sunday, February 12, 2012

መመለስ አቃተኝ!

 ጠያቂ፦ አብርሃም እባላለሁ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል አምናለሁ፡ ቃሉንም ዘወትር አነባለሁ፡ ነገር ግን በአሳፋሪ የዝሙትና የስንፍና ሃጢአት ባሪያ ሆኝለሁ....ብዙ ጊዜ ለመመለስ ብሞክርም በተደጋጋሚ ወደቅኩ። እባካችሁ ይህንን ጥያቄ ያነበባችሁ ሁሉ ባላችሁበት ቦታ ጸልዩልኝ። ምክራችሁንም ለግሱኝ።
 መልስ፦
የዝሙት ኃጢአት ባሕርያት

ከሁሉ አስቀድሜ እየተለማመድክ ስላለኸው ኃጢአት ምንነትና ባህርይ የበለጠ መረዳት እንድትችል አንዳንድ ነገሮችን ለማለት እወዳለሁ።

እንደዚህ አይነት ኃጢአቶች ብዙ ጊዜ በትንሹ የሚጀመሩና ከጥቂት ጊዜ በኋላ የራሳቸው የሆነ ሕይወት አበጅተው በራሳቸው ጉልበትና ኃይል የሚንቀሳቀሱ ኃጢአቶች ናቸው። ብዙ ጊዜ የሚጀመሩት በፈተና ነው። የሚፈትኑና የፍትወት ፍላጎትን የሚያነሳሱ ሁኔታዎች ይገጥሙና የመጀመሪያውን ፈተና መቋቋም ባለመቻል ይጀመራል። ብዙ ጊዜ ይህንን አይነት ኃጢአት የሚለማመድ ሰው (ቀድሞውኑም ጤናማ የክርስትና ሕይወት የነበረው ሰው ከሆነ) ኃጢአቱን ለማሸነፍና ፈተናውን ለመቋቋም የተወሰኑ ትግሎችን ያደርጋል። የሚፈትን ነገር ይኖራል፤ እናም ያንን ለመቋቋም ይሞከራል፡ ነገር ግን ይወደቃል። እንደ ማንኛውም ኃጢአት ከመደረጉ በፊት የነበረው "ደስታ"ና ግፊት ኃጢአቱ ከተደረገ በኋላ ከመቅስበት ጠፍቶ ወደ ጸጸትና ሃፍረት ስለሚለወጥ፤ ፈተናውን ሳይቋቋሙ ቀርተው በዚህም ኃጢአት ሲወድቁ ሰዎች በመጀመሪያ አካባቢ ይጸጸታሉ፤ ሁለተኛም ደግመው ላለማደረግ ይወስናሉ። ነገር ግን ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ተመሳሳይ ፈተና ይመጣል፤ ትንሽ ያንገራግራሉ ደግመውም ያንኑ ኃጢአት ሲለማመዱ ራሳቸውን ያገኙታል ወዘተ።

እንዲህ እንዲህ ይልና መጀመሪያ ፈተና ከዚያም ማንገራገር በመጨረሻም መውደቅ የሚለው አዙሪት እየተደጋገመ ይሄዳል። ይህ ድግምግሞሽ ግን ወደሚቀጥለው የኃጢአት ደረጃ ይሻገራል። ይህም ከጊዜ በኋላ ኃጢአቱ እየተወደደና እየተደጋገመ ስለሚሄድ በራሱ ሕይወት ያለው ልምድ ይሆናል። ልምድ ደግሞ የሕይወት አካል ከሆነ ኃጢአቱ የሚደረገው ፈተና ስላለ ብቻ ሳይሆን ደስ ስለሚልና ስለ ለመድነው ነው። ከፈተና አልፎ የራሱ የሆነ ሕይወት አበጀ ማለት ነው። ከፈተና አልፎ በየጊዜው የምንለማመደው የሕይወታችን አካል ሆነ ማለት ነው። በዚህ ደረጃ ከደረሰ ደግሞ ኃጢአቱን ለመለማመድ ግዴታ የሚፈትኑ ነገሮች መኖር የለባቸውም። እኛው ራሳችን፤ በራሳችን ተነሳሽነት እንደ ልማዳችን ኃጢአቱን መለማመድ እንጀምራለን። መጀመሪያ ላይ ፈተናው የሚመጣው ከውጪ ነበር፤ በኋላ ልምድ ሲሆን ግን ያለ ወጪያዊ ፈተና ኃጢአቱ መጥፎ ልማድ ስለሆነብን ተነሳሽነቱ ከእኛው ውስጥ ነው የሚመነጨው። ይህ አደገኛ አካሄድ ላይ እንዳለን የሚያሳይ ምልክት ነው። ኃጢአቱ በሕይወታችን ቤቱን እየሠራና የእኛ አንዱ አካል እየሆነ የሚያመልክት ትልቅ ማስጠንቀቂያ ነው

ያልገባኝ ነገር አለ!

ጥያቄ፦ እኔ ያልገባኝ ነገር አለ፤ እሱም ጌታ ፍቅር ነው እና ኃጢአት የሚሠራ ሥጋ ነው እና እሱ ራሱ ካልቅደሰኝ እንዴት ራሴ ልቀደስ እችላለሁኝ? ራሴ የምቀደስ ከሆነ ሕግ ይሆንብኛል እና እወድቃለሁ። አታድርግ ከሆነ ሰው በኋላ አይበርታም፡ ሰለዚህም ግራ መጋባት ላይ ነኝ።
 መልስ፦
ጸጋና ኃጢአት

በቅድሚያ አዲስ ኪዳን ስለ ሁለት ኃጢአቶች ይናገራል። አንደኛው ሳናውቅና ሳናስብ አንዳንዴ ስለምናደርገው ኃጢአቶች። እንደዚህ ያሉትን ኃጢአቶች ካደረግን፤ ንስሐ ገብተን ኃጢአታችንን እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለን ተጽፎአል።

Quote:
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1
8 ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
9 በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።

Saturday, February 11, 2012

የጤናማ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ!

ጠያቂ፦ ስለኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ዶክትሪን ብታስረዱኝ?

መልስ፦
በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት አሉ። የእያንዳንዳቸውን ዶክትሪን ልዩነት ለመጻፍ አስቸጋሪ ነው። ቢሆንም ግን አንዲት ቤተ ክርስቲያን ጤነኛ መሆንዋን የሚያመለክተን ዶክትሪንዋ (አስተምህሮትዋ) ነው። ጤነኛ ዾክትሪን ያላትን ቤተ ክርስቲያንን ለመለየት የሚከተሉትን መስፈርቶች መጠቀም ያስፈልገናል፦

1. ስለመጽሐፍ ቅዱስ ያላት አመለካከት ምን ነው - Bibliology
- መጽሐፍ ቅዱስ የ እግዚአብሔር ቃል ነው ብላ የማታምን፤ እንዲሁም ለቀደመው ዘመን እንጂ ለዚህ ዘመን አልተጻፈም ብላ የምታምን ከሆነ ወይንም ከመጽሐፍ ቅዱስ ሌላ አግንና የምትጠቀምበት ሌላ አይነት መጽሐፍት ያላት ከሆነ ይህች አይነቱ ቤ/ክ ጤናዋ ትክክል አይደለም። ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ሌላ ነገር የምታስተምር ከሆነ መስመር የሳተች ናት።
2. ሰለ ስነመለኮት (ስለ እግዚአብሔር) ያለት አስተምህሮት ምንድነው? - Theology
- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በሦስትነት አንድነትን የማታስተምር ከሆነች ጤነኛ አይደለችም።
3. ስለ ክርስቶስ ያላት እምነት ምንድነው?- Christology
-ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑን የምታምን ቤ/ክ ጤነኛ ቤ/ክ ናት
4. ስለመዳን ያላት እምነት ምንድነው? እንዴትስ ይዳናል ብላ ታምናለች? - Soteriology
- በክርስቶስ ከማመን ውጪ ሌላ ወይንም ተጨማሪ የመዳኛ መንገድ የምታመለክት ቤ/ክ ጤነኛ አይደለችም።
5. ስለመንፈስ ቅዱስ ምን ብላ ታምናለች? - Pneumatology
- መንፈስ ቅዱስ ከስላሴ አካላት አንዱ እንደሆነ ፣ ለቤተ ክርስቲያንን በሃይል የሚያጠምቅ፣ወደ እውነት የሚመራና አስተማሪ መሆኑን ወዘተ. የምታምን ቤ/ክ ጤነኛ ናት።
6. ስለመላዕክት ምን ብላ ታምናለች? - Angelology
- መላዕክት የእግዚአብሔር ፍጥረትና አገልጋይ መልዕክተኞች እንደሆኑ እንጂ አማላጅ እንዳልሆኑ የምታምን ቤ/ክ ጤነኛ ናት። መላእክት ከምድር እስከሰማይ በተዘረጋው መሰላል ላይ ይወጣሉ፣ ይወርዳሉ እንጂ ራሳቸው መውጪያና መውረጃ መሰላል አይደሉም። ናቸው የምትል ከሆነ በክርስቶስ ቦታ መላእክትን ተክታለችና ጤናማ አይደለችም።
7. ስለርኩሳን መላዕክትስ ምን ብላ ታምናለች - Demonlogy
- ርኩሳን መናፍስቶች የ እግዚአብሔርን አላማ አሰናካዮች፣ የሰውም የ እግዚአብሔርም ጠላቶች እንደሆኑ፤ በመንፈስ ቅዱ ኅይል በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከሰዎች መውጣት እንዳለባቸው የምታምን ቤ/ክ ጤነኛ ናት። ከክፉ መናፍስት መካከል ክርስቲያን መሆን የሚችሉ እንዳለ የምታስተምር ከሆነ ጤናማ ቤ/ክ አይደለችም።
8. ስለቤተ ክርስቲያንስ ምን ብላ ታምናለች - Ecclesiology
- ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል፤የክርስቶስ ሙሽራ የምታምን ቤተ ክርስቲያን ጤነኛ ናት።
9 ሰለመጨረሻው ዘመን ምን ብላ ታምናለች? - Eschatology
- ቤ/ክ እንደምትነጠቅ፣የመከራው ዘመን  በምድር ላይ  እንደሚመጣ የምታምን፣ ከክርስቶስ ጋር እንደገና በክብር እንደምትገለጥና  ከንጉሡ ጋር በክብር ነግሳ እንደምትኖር የምታምንም ቤ/ክ ጤነኛ ቤ/ክ ናት።

እንግዲህ የዶክትሪን ልዩነቶች ከላይ በተጠቀሱት ዙሪያ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ሊኖር ይችላል። በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያን ውስጥ በአብዛኛው ተቀራራቢ መረዳት አለ ብዬ አምናለሁ። በዚህ ምሳሌ ነገሬን ልደምድም.... ጊታር የሚጫወቱ ሰዎች ይህ ምሳሌ በቀላሉ ይገባቸዋል። ጊታር ስድስት ክሮች አሉት የሁሉም ድምጽ ይለያያል። ሁሉም አይጠብቁም ሁሉም ደግሞ አይላሉም። ከሚገባው በላይ የጠበቀ ድምስ ዲስኮርድ ይፈጥራል፤ ከሚገባው በላይም የላላ እንዲሁ። በዶክትሪንም ዙሪያ ከላይ የዘረዘርኩት የሚጠብቁ ናቸው.... ይህንን ማላላት አይቻልም። ስለዚህ የሚጠብቀውን አጥብቀን የሚላላውን እናላላ። በሚያጨቃጭቁ ዶክትሪን ዙሪያ ከመናቆር አንድነታችንን ጠብቀን ወንጌልን እናሩጥ!
ከኢየሱስ.ኮም ድረገጽ የተገኘና በጥቂት ማስተካከያ የቀረበ