Wednesday, May 13, 2015

I.S የተባለው ሽብርተኛ ቡድን አቀንቃኝ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ!

በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን ተደጋጋሚ የሃይማኖት ጥቃት ሲፈፀም ቆይቷል። ችግሩ እየተባባሰ እንጂ እየቀነሰ ሊሄድ አልቻለም። የኦሮቶዶክስ እምነት ተከታዮች እየተሰቃዩ ነው። ቤተ ክርስቲያናቸው ተቃጥሏል። የግለሰቦች ንብረት ወድሟል። "ሀገሩን ለቃችሁ ካልሄዳችሁ እንፈጃችኋለን"ማለት ከተጀመረ ሰነባብቷል። የመከራውን ገፈት ቀማሾች ለአቤቱታ በሄዱበት መንግስታዊ እርከን ሁሉ የሚጠብቃቸው ሹም ራሱ የሽብር አስፈጻሚ አካል ነውና "ከሚገድሏችሁ ለቃችሁ ሂዱ" የሚል ምላሽ እየሰጡ ይገኛሉ።
ከእግዚአብሔር በታች የሕዝብ ከለለሰ መንግሥት ነው። ሕግና መንግሥት ባለበት ሀገር ሕዝብ የመኖር ዋስትናውን በአሸባሪዎችና ለሽብርተኞች ከለላ በሚሰጡ አመራሮች ህልውናውን ሊያጣ አይገባም። ኢህአዴግ ለእንደዚህ ዓይነት ተግባርና አመራር ትእግስት ሊኖረው እንደማይገባ አበክረን እንጠይቃለን። " ሳይቃጠል በቅጠል" እንዲሉ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ የህዝብ አለኝታነቱን ሊያሳይ ይገባል። ሕዝቡ የድረሱልን ጥሪውን በደብዳቤ አቅርቧል።
" የመንግሥት ያለህ!!!"