አቶ የኑስ (ዮናስ) የተባሉት - በመጽሐፍ ቅዱስ) ላቀረቡት የግል ወቀሳ፤
አቶ ዮናስ !!!
አሁንም
ስላም ይብዛልዎት እያልኩ ነገርን ነገር ያነሰዋልና ባላሰብኩት ነገር ላይ በሰነዘሩብኝ የሃሰት ክስ ላይ ተመስርቼ አንዳንድ የጋራ ጥያቂዎችን እንዳቀርብ ይፍቅዱልኝ???
1) የሙስሊሙ ጥያቄ በአገሪቱ ውስጥ በሙሉ መልካም አስተዳደር እንዲመጣ ነው ወይስ በእኛ ላይ ብቻ በደል ስለደረሰብን ትግላችን ለሙስሊሙ መብት ብቻ የሚል ነው?
2) በየቦታውና በየጊዜው በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ዘዎትር የሚሰማው መፈክር 'መሪዎቻችን ይፈቱ' እንጂ በታሰሩ ጋዜጠኞች፤ ፖለቲከኞች፤የመብት ተከራካሪዎችና በአጠቃላይ ፍትህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ስትሉ ሰምቼ አላውቅምና ይህ ከምን የመጣ ነው?
3) ያስታውሱ እንደሆነ ''ሰማያዊ ፓርቲ'' ባዘጋጀው ሰልፍ ላይ አዘጋጆች ከተከሰሱበት ምክናያት አንዱ በሰልፉ ላይ አንዳንድ ሙስሊም ወገኖች ባቀረቡት ጠበብ ያለ ግለኛ መፈክር ምክንያት ነበር ታዲያ በቅንነት ለአንድ አገርና ሕዝብ በተሰለፈ ሁሉን አቀፍ ሰልፈኛ መካከል እንዲህ ዓይነቱ ሥራና ዝንባሌ የት የሚያደርሰን ይመስልዎታል?
4) ጥያቄዎቼ የሁላችንንም የወደፊት የጋራ ጉዳይ የሆነውንና አገርን ለመልካም አስተዳደር ለማብቃት ከሚደረገው አጠቃላይ እንቅስቃሴ አንጻር ሊኖረው የሚገባውን ፋይዳ ከወዲሁ ቆም ብለን ለማሰብ እንድንችል በማሰብ የተሰነዘሩ መሆናቸውን ከወዲሁ አስበው በቅንነት እንዲመልሱልኝ በኢትዮጵያዊ ጨዋነት በትህትና እየጠየኩ ባለፈው እንደነካኩት እንደ ሃይማኖት ልዩነትና ክርክር አድርገው የሚቆጥሩት ከሆነ ግን ለፍላጎትዎ ማርኪያ የሚሆንዎን ጥሩና መሰረት ያለው ክርክር ወይም በመረጃ የተደገፈ ማስረጃ በክርስትናና በእስልምና መካከል አገሪቱ ባፈራቻቸው ምሑራን በአማርኛ በስፋት የሚቀርበውን ''Аnswering Islam '' ድህረ ገጽ ቢከታተሉ ለችግርዎ የተሻለ መልስና ግንዛቤ ሊያገኙ ይችላሉና ትኩረትዎን ወደ እዚህ ድህረ ገጽ ቢያደርጉ ይሻልዎታል ማለት እወዳለሁ። ለአገራችን ጠቅላላ ችግር ብዙ የሚሠራ ሥራ ስላለ እኔን ለጊዜው ቢተውኝ??? አሁንም ጨዋ ሙስሊም ወገኖቼን እወዳለሁ። ክፋትን ተላብሰው ባልሆነ ነገር በመካፋፈል ለትውልድ መርዝ የሚረጩትንና እየረጩ ካሉ የእኛው ጉዶች ጋር ግን ምንጊዜም ስምምነት እንደሌለኝ ላሳውቅዎት እወዳለሁ። ደግሞም አንዳንዶች በመድረክ ላይ እየወጡ ''አላህ ወ-አክብር'' እንደሚሉት ዓይነት ማስመሰል ጨርሶ አላውቅበትምና በዚህ አይገምቱኝ። ደግሞም የእኔን እምነት መከተል አለባችሁ በማለት ከፍቅር ሌላ ሰይፍ አላነሳም። ሰይፍ የሚያነሱ በሰይፍ ስለሚጠፉ!!!
አሁንም ለጋራ የአገራችን ችግር
በጋራ አብረን በቅንነት እንሰለፍ!!!
ምድራዊ አገራችንን ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ያስባት!!!
አሁንም አክባሪዎ
በይስሃቅ በኩል የአብርሃም ዘር
ተናገር ነኝ