Friday, March 29, 2013

የአርማጌዶን ዘመን ቀርቧል?


ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።
እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።
በዕብራይስጥም አርማጌዶን ወደሚባል ስፍራ እስከተቱአቸው።



Thursday, March 28, 2013

የጅማ ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ አባ ማቴዎስ ታምሩ የገቡበት አልታወቀም !

          
                  source: http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com
 "ማኅበረ ቅዱሳን" አፍኖ እንደወሰዳቸው ይጠረጠራል"

የጅማ ቅዱስ ሚካኤል አስተዳዳሪ አባ ማቴዎስ ታምሩ የገበቡበት አለመታወቁን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ አባ ማቴዎስ ታምሩ በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከ"ማኅበረ ቅዱሳን" ተከታታይ የሆነ ጥቃት እንደደረሰባቸው ሲታወቅ፣ እርሳቸውም "ማቅ" የአጥቢያ ቤተክርስቲያኑን መዋቅር በመቆናጠጥ ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን የሚያደርገውን ሕገ ወጥ አካሄድ በመቃወም ረገድ ብርቱ እንደነበሩ ተመስክሮላቸዋል፡፡
ይሁን እንጂ "ማቅ" አንድ ጊዜ ያተኮረበትን ቦታና ሰው እስኪቆጣጠር ዕረፍት የሌለው በመሆኑ አባ ማቴዎስን ሌት ተቀን መነዝነዝና ስቃይ ማብላትን ሥራዬ ብሎ መያያዙን ታዛቢዎች ገልጸዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ አባ ማቴዎስ በራሳቸው ጊዜና ፍላጎት ዕረፍት ለማድረግና ዘመዶቻቸውን ጠይቀው ለመምጣት ወደ ሲዳማ ዞን አርቤጎና  ወረዳ መሄዳቸው ታውቋል፡፡


እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ

                                        
                       (የጽሁፉ ባለቤቶች ለእስልምና መልስ አዘጋጅዎች ነው)
( ክፍል ሦስት )

መሰረታዊና ታሪካዊ ጥያቄ፡

የሼክ አብደላ ርዕዮተ ዓለም በሌላው ዓለም ውስጥ ተቀባይነት ሲያገኝና ዓለም አቀፍ ሲሆን በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዘንድ  ተቀባይነት ስለምን ሊያገኝ አልቻለም? ይህ ጥያቄ በኢትዮጵያውያን መካከል መነሳትና መብላላት ያስፈልገዋል፡፡ ይህ ጥያቄ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሁሉ ሊጠየቁበት የሚገባው ጥያቄ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ጥያቄው በምንም መልኩ ቢላመጥና ቢገላበጥ የሚሰጠው መልስ ከሚከተሉት ከሁለቱ መልሶች መካከል ከአንዱ በፍፁም ሊዘል አይችልም፡
አንደኛ፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የእስልምና እምነት በጣም ጥንታዊ ወይንም የተለምዶ ብቻ ስለሆነ ነው፡ አል-አሕበሽን አይቀበልም፤ ወይንም፤
ሁለተኛ፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ስር የሰደደውና ብዙዎች የሚከተሉት የእስልምና እምነት ርዕዮተ ዓለም የዋሃቢው አክራሪ እስልምና ስለሆነ የአል-አሕበሽን ትምህርት አይቀበልም የሚሉት ብቻ ናቸው፡፡
እንግዲህ በአሁኑ ጊዜ የተነሳው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በማነው የተነሳው፣ ማን መራው፣ ዓላማው እና የወደፊት ግቡ ምንድነው የሚሉት ሁሉ መልሳቸውን የሚያገኙት ከዚህ መሰረታዊና ታሪካዊ ጥያቄ ጋር ተያይዘው ሲታዩ ብቻ ነው፡፡ ይህ ነጥብ ነው ለምናደርገው ነገርና ለምንሰጠው ድጋፍ ጥንቃቄ እንድናደርግ የሚጠራን፤ ይህ ነጥብ ነው ዛሬ ተቀምጠን የሰቀልነው ነገ ቆመን የማናወርደው እንዳይሆን የሚመክረን፣ ይህ ነጥብ ነው የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው የሚለውን አባባል አቁመን አሁን አርቀን ለማሰብ መነሳት አለብን የሚለን፡፡

የአል-አሕበሽ መሰረታዊ እምነቶች

የአል-አሕበሽ መሪ ሼክ አብደላ ለተከታዮቹ ካደረጋቸው ንግግሮች ውስጥ በአንዱ እንቅስቃሴው የሚከተለውን መሰረታዊ ርዕዮተ ዓለም ለማስቀመጥ እንደሞከረና በዚያም ውስጥ ከዋነኛው ተቃዋሚ እራሱን ለይቶ እንዳስቀመጠ ፕሮፌሰሮቹ አመልክተዋል ንግግሩም፡-
 “እኛ እስላማዊ ማህበር ነን፣ (ማህበራችን) የሚወክለውም ምንም ዓይነት የፈጠራ ልዩነት የሌለበትን ነው፣ ማለትም እንደነዚያ ከሃምሳ፣ ሁለት መቶ ወይንም ስድስት መቶ ዓመታት በፊት እንደተጨመሩት ዓይነት አይደለንም፡፡ የመጀመሪያዎቹ የሳይድ ካታብ ሐሳቦች ናቸው ... ሁለተኛዎቹ ደግሞ የመሐመድ ኢብን አብድ አል-ዋሃብ ናቸው፣ ሦስተኛዎቹ ደግሞ  የኢብን ታይሚያ ናቸው ከእነዚህ ነው አብድ አል-ዋሃብ ሐሰቦቹን ያመጣቸው፡፡ (የወሰዳቸው)፡፡ እኛ ግን አሻሪስ እና ሻፊዎች ነን፡፡ የእምነታችንም መሰረት አሻሪያ ሲሆን ሻፊያ ደግሞ የየዕለቱ መለያችን ነው፡፡” የሚል ነበር፡፡
በንግግሩ ውስጥ የጠቀሳቸውን ሰዎች እንደ ዋነኛ ጠላቶች አድርጎ ለምን እንደመረጣቸው እና ምክንያቱንም ሊቃውቱ ሲያስረዱ የሚከተሉትን ከታሪክ አቅርበዋል፡ ሳይድ ኩታብ የግብፅ እንቅስቃሴ መሪና ሊቅ ሲሆን፣ በእስልምና የፖለቲካል ሐሳቦች ላይ ሥራን በመስራት በሙስሊም ወንድማማችነትና በዋሃቢዝምን መሰረታዊ ነጥቦች መካከል ድልድይ የሰራውን መጥቀሱ እንደሆነ፡፡ ሼኩ አል-ዋሃብን እና ኢብን ታይሚያምን ሲጠቅስ ደግሞ የዋሃቢዝም መስራችና የትምህርቱ ታሪካዊ አነሳሽንና ምንጭን ማለትም ግልፅ የሆነውን ነገር ማንሳቱ ነበር ይላሉ፡፡ ኢብን ታይሚያ የ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ሊቅ ነበር፡፡ ዘመናዊው የፓኪስታን ፈላስፋ አቡ አል-አላ አል-ማውዱዲ የተነሳሳው በኢብን ታይሚያ እና በሳይድ ኩታብ በተሰጠው በዋሃቢያ ትምህርት ነው፣ እርሱም የሙስሊም ወንድማማቾችን የሃይማኖታዊ ሕጋዊነት በመስጠት ከ1960 ጀምሮ ወደ አክራሪ እንቅስቃሴነት የመቀየር ህጋዊነት አምጥቷል ይህም እስላማዊ ያልሆኑትን እና መሰረታዊ ያልሆኑትን ትምህርቶችና ነገሮች በማስወገድ እስልምናን ለማጥራት ተብሎ ነበር፡፡ የአል-አሕበሽ መሪ እነዚህን አስተማሪዎችና መሪዎች ከታሪካዊ አስተምህሮአቸው በመነሳት የጠቀሰበት ዋናው ምክንያት እዚህ ላይ ግልፅ ነው፣ እርሱም እነርሱ በሙሉ ያራምዱት የነበረው እስልምና ከሌሎች ጋር በሰላም ለመኖር የሚፈልግም የሚችልም እንዳይደለ ነው፡፡