Wednesday, April 18, 2012

ሀልዎተ እግዚአብሔር



ርእስ፤ ሀልዎተ እግዚአብሔር/Existence of God/
ደራሲ፤  ካሳሁን ዓለሙ
መግቢያ

20ኛው // ከየትኛውም የታሪክ ጊዜ በበለጠ ሳይንሳዊ ዕውቀት የመጠቀበት ክፍለ ዘመን እነደነበር ይታወቃል፡፡ ዘመኑ ሳይንሳዊ አስተሳሰብ የመጠቀበት ብቻ አልነበረም፤ በተቀራኒውም ዓለም በጦርነት የታመሰችበትና በኢ-ሞራል አስተሳሰብ የዘቀጠችበትም እንጂ፡፡ በተለይ -ሞራላዊነት ያደረሰው ጥፋት ወደርና ልክ የለውም ሊባል ይቻላል፡፡ ለዚህ ደግሞ የዘመኑ ፍልስፍናዊ አስተሳሰብ በቁሳዊ አመለካከት ላይ መመሥረቱና መንፈሳዊ የሚባሉትን የሰው ልጆች ሀብታት መሰረዙ ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ ይህ መንፈሳዊ አመለካከትን በሐሣባዊነት ቅርጫ አጉሮ የተመሠረተ ፍልስፍናም የሣይንስን ዕድገት በቁሳዊነት መርህ ብቻ እንዲመራ አድርጎታል፡፡ በዚህ የተነሣ ሃይማኖትም ተጠራርጎ በሐሣባዊነት መርህ በመፈረጅ የሳይንስ ፀር ተደርጎ ሊወሰድ ችሏል፡፡ ይህ መርህ በተለይ 2ኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ዓለም በሶሻሊዝም አስተምህሮ ተጠምቃ አዲስ እግዚአብሔር የለምትምህርትንክርስትናእንድትነሣ አድርጓታል፤አዲስ ክርስቲያን ከጳጳስ ይበልጣልእንደሚባለውም በአዲሱ አስተሳሰብ ተጠምቀው ሳይንቲስት የኾኑት የቁሳካላዊያን ልጆችም እግዚአብሔር የለምአስተምህሯቸው ውጥንቅጧን አውጥተዋታል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያም የገፈቱ ቀማሽ በመኾን አዲሱን ሃይማኖት ተቀብላ እንዲትጠመቅ የተማሩትምሁር ልጆቿበግልፅም በሥውርም ጥረውላታል፡፡ በዚህ ጥረታቸውም የሀገሪቱን ትምህርት በቁሳዊ ሳይንስ የአስተምህሮ መርህ በመቅረጽ፣ የሃይማኖትን የሥልጣኔ ፀርነት በሥርዓተ-ትምህርቱ በማራገብና የመንግሥት ተቋማትን ተቆጣጥረው በማስተማር ወትውተዋል፡፡ በዚህም ያልገባቸውን አዲስ የቁስአካላዊ አስተምህሮ በትውልዱ አዕምሮ አጭቀው አጭቀው ግራ ገብ ስላደረጉት ጭራሽ ለባሰው ምንፍቅና እኔ አምላክነትትምህርተ ዕምነት ሰለባ አድርገውታል፡፡ በዚህ የተነሣ እነ ኦሾ እንኳን እንደፈጣን ሎተሪበነፃነት እየፋቁት ይገኛሉ፡፡ ከዘመኑ ትውልድም ብዙ ወጣትኒቼ እንዲህ ብሏልሲሉት የእሱ አቀንቃኝ፣ ኦሾን ሲሰማም የእሱ ደቀ መዝሙር፣ ሪቻርድ ዳዊኪንምእግዚአብሔር ቅዠት ነውሲለው ቅዠታም፣ የእስጢፋኖስ ሃውኪንግን አዲስ የሳይንስ ግኝት ሲሰማ ወይም ሲያይም -አማኝ ሳይንቲስ ይኾናል፡፡ ይህ ብቻ ሳይኾን የቁሳካላዊ ዝግመተ ለውጥ አስተምህሮ የፈጠረበት የሥነ ምግባር አልባነት ተፅእኖም -ሞራላዊሙሱንእንዲኾን አድርጎታል፡፡

ከፈጣሪ አይደለም

        እግዚአብሔር ፍቅር ነው!
ሲለጉን ተደፋን፣ ሲገርፉንም ጮኽን
ሲስቡን ተሳብን፣ ሲገፉን ተገፋን
ሲመቱን አመመን፣ ሲጥሉን ወደቅን
ሲሰብሩን፣ደቀቅን፣ሲገድሉንም ሞትን
እንደሆነው ሆነ፣ የሆነው ሆነብን፣
 ከቶ ምንም የለም፣ ያልሆነው የሚሆን።
                 ከሆነውም ሁሉ፤ የሆነብን ነገር፣
                ሥረ መሠረቱ፣ የኩነቱ ምስጢር
               የክስተት እንግዳ፣ ድንገት የሚፈጠር
               ከፀሀይዋ በታች ከቶ አዲስ ነገር
             አምላክ ያላወቀው የለም በዚህ ምድር።

Sunday, April 15, 2012

መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንላችሁ!!!



 "ክርስቶስ ተንስአ እሙታን፣በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን'
 አሠሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፣
ሰላም' እምይእዜሰ፣ ኮነ ፍስሐ ወሰላም"