Tuesday, March 7, 2023
ኬንያዊው "ኢየሱስ ክርስቶስ" ችግር ላይ ወድቋል‼
"ከ2000 አመታት በፊት በኢየሩሳሌም የነበርኩት ትክክለኛው ኢየሱስ እኔ ነኝ" የሚለው ኬንያዊው ፓስተር ሙአሊሙ የሱ ዋህ ታንጎሌ በኬንያ በርካታ ተከታዮችን አፍርቷል።
አንድ ሚስት እና ስምንት ልጆች ያሉት ሙአሊም ተዓምራቶችን ሲፈጽም አይተናል በሚሉ በሺህ የሚቆጠሩ ተከታዮች ታጅቦ ሥርዓተ አምልኮ ያስፈፅማል።
12 ደቀመዝሙሮችን ሳይቀር የሰየመው እና "ዓለምን ለማዳን ከእግዚአብሔር የተላኩ መሲህ ነኝ" የሚለው ሙአሊም በሽተኞችን ከመፈወስ አንስቶ በሠርግ ላይ ውሃን ወደ ሻይ ሲቀይር አይተናል ይላሉ ተከታዮቹ።
ተከታዮቹ የቡግማን ሰዎች ታዲያ መጪው ፋሲካ ከመድረሱ በፊት ትክክለኛው መሲህ መሆኑን ለማረጋገጥ የፈለጉ ይመስላል።
ይህንን መሲህ ነኝ ባይ ፓስተር "እንሰቅለው ዘንድ ይገባል። ከዚያም በ3ኛው ቀን ከሞት ይነሳ እንደሆነ ማረጋገጥ አለብን።" በማለት ውሣኔ ላይ ደርሰው ዝግጅታቸውን ጀምረዋል።
አሟሟቱም በመስቀል ላይ በሚስማር ተቸንክሮ እንዲሆን እና ከቀበሩት በኋላ ቀጣዩን 3 ቀናት ከሞት ይነሳ እንደሆነ ለመጠበቅ ወስነዋል።
ይህንን የተረዳው እና ሃሳባቸው ምንም ያልጣመው ሙአሊም ወደ ኬንያ ፖሊስ በመደወል ከስቅላት እንዲያስጥሉት ተማጽኗል።
ተከታዮቹ ግን በውሳኔያቸው ጸንተዋል፣"ፖሊስ በእምነታችን ጣልቃ እንዳይገባብን!! ይህ በእኛ እና በመሲሑ ሙአሊም መካከል የምንጨርሰው ጉዳይ ነው" ብለዋል!!
ጋሼ ሙአሊም አላህ ይረዳህ እንደሆነ እስኪ ወደዚያ ጩህ!
Subscribe to:
Posts (Atom)