ከዚህ በፊት አንድ አንጋፋ ፖለቲከኛ፣ ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው ድርጅት “የቤተ ክህነቱ እዳ ነው” በማለታቸው በማቅ መንደር አቧራው ጨሰ ማሰኘቱ
አይዘነጋም። ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትርም “ማቅ፣ሰለፊያ መሰል ማኅበር ነው” በማለታቸውም ብዙ ጊዜ የማኅበሩ
ስውር ልሳኖች ወይም አፍቃሬ ማቅ እንደሆኑ ከሚታሙት የሀገር ቤት
መጽሔቶችና ጋዜጦች አንስቶ እስከ የመረጃ መረብ ድረ ገጾች ድረስ ማቅ እንዴት ተነክቶ? የሚል ጩኸት በአንድነት አስተጋብተው
ነበር። የማኅበሩ የጡት አባት የሆነው የሜሪላንዱ ሰውዬ ደግሞ እንባ
ቀረሽ ጽሑፍ በማቅረብ የማኅበሩን ቅዱስ መሆን በመለፈፍ ለማሳመን ብዙ መጣሩን እናስታውሳለን። ማኅበሩ ያሰማራቸውና በፍቅሩ የወደቁለት የጋሪ ፈረስ የመጦመሪያ ድረ ገጾችም ስለማኅበሩ ቅድስና
በተጠራው የምስክርነት ለቅሶ ላይ የቻሉትን ያህል የሀዘን እንባ ጽሁፍ በማቅረብ
ትብብራቸውን አሳይተዋል። ማኅበሩ ከሰፈረበት የአሸባሪነት የመንግሥት /Black list/ ጥቁር መዝገብ ላይ ባያሰርዘውም ጊዜ ለመግዛትና መንግሥት ሊያፈርሰን ነው ከሚለው
ፍርሃት ለጊዜውም ቢሆን መጽናኛ ሆኗቸው ማለፉ አይዘነጋም። የማቅ አልቃሾችን የአዞ እንባ ጽሑፍ ተከትሎ የማኅበሩን ዐመል በደንብ የመረመሩ ጸሐፊያንም “ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክህነቱ እዳ” በሚል ርእስ መጽሐፍ አሳትመው ማኅበሩ ቅዱስ እንዳልሆነና በቅዱሳን ሽፋን ተሰባስቦ የራሱን አጀንዳ
የሚያራምድ የእውነት ሁሉ እንቅፋት መሆኑን የሚያስረዳ
ጽሁፍ ለንባብ በማብቃት አስነብበውናል።
እኛም የተናጋሪ ፖለቲከኞችንም ይሁን የጸሐፊያኑን ማንነት ትተን በማቅ ዙሪያ የሚነገሩትንንና የተነገሩትን ልብ ብለን ብንመለከት ከማኅበሩ ጠባይ አንጻር የምንደርስባቸው እውነታዎች መኖራቸው በምንም መልኩ የሚስተባበሉ አይደሉም። ለመሆኑ ማኅበረ ቅዱሳን ማነው? የቅዱሳን ማኅበር የሚባለው የማኅበሩ አባላት ራሳቸው ናቸው ወይስ ስማቸው
ያልተገለጸ ቅዱሳን? ከማኅበሩ ጠባያት አንጻር ብዙ ማለት የሚቻል ቢሆንም ስለ ቅድስናው ትተን ከዓላማው አንጻር ጥቂት አመክንዮታዊ
ነጥቦችን እናንሳ።
የገጽታ ግንባታውን በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ውስጥ መዘርጋት፣
1/ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንበረ ፓትርያርክ አንስቶ እስከ አጥቢያ
ቤተ ክርስቲያን ድረስ ወጥ የሆነ መዋቅር እንዳላት ይታወቃል። ማኅበረ
ቅዱሳን ደግሞ በዚህ መዋቅር ውስጥ የታቀፈ ነገር ግን ራሱን የቻለ አንድ ተቋም ነው። ከመንበረ ፓትርያርክ ጀምሮ እስከ
አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ ራሱን አክሎ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱን መስሎ ተደራጅቷል። የቤተ ክርስቲያኒቱን አባላት ለራሱ አባልነት
ይመለምላል። ዐውደ ምሕረቷን ይጠቀማል። ከማእከል ወደ አጥቢያ የሚወርዱ መመሪያዎችን ያስተላልፋል፣ በማኅበሩ ንድፈ ሃሳብ /Theory/ የተጠመቁ ምልምል መምህራንን በስብከተ ወንጌል ስም ይልካል። በየአድባራቱ፣ ዩኒቨርሲቲውና
ኮሌጆቹ ውስጥ የማኅበሩ ስም በወጣቱ ልብ ውስጥ እንዲሰርጽ አጥብቆ ይሰራል። ይህም ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተጠሪና ጠበቃ እንደሆነ
ለማሳየት የሚከወን የመንፈሳዊነት የስም ግንባታ ሥራ መሆኑ ነው።
በቤተ ክርስቲያኒቱ ባለ ሥልጣናት መጠቀም፣
2/ ራሱን አክሎና ቤተ ክርስቲያኒቱን መስሎ ለመንቀሳቀስ ይችል
ዘንድ የጳጳሳቱን ማንነት ለራሱ ጥቅም በመጠምዘዝ፣ በመደለል፣እንዲሁም ቅዱስ በመምሰልና እውነተኛ እንደሆነ በውስጣቸው የማንነት
ምስሉን በማስቀመጥ ተቀባይነት እንዲኖረው የውዴታ መልካም ፈቃዳቸውን
ይቀበላል። የማይቀበሉት ካሉ ደግሞ ራሱም ይሁን በአገልጋዮቹ በኩል ይዘምትባቸዋል። በየደረሱበት ሁሉ ይቃወማቸዋል።/እንደ አቡነ ፋኑኤል ያሉትን፣ ከደቡበ ኢትዮጵያ ጀምሮ
እስከ አሜሪካ እንዴት እግር በእግር እየተከታተለ ሲዋጋቸው
መቆየቱን ልብ በሉ!!/
በሚቀበሉት ጳጳሳትና የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጆች የተነሳ ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያኒቱ ባለችበት ሁሉ ህልው ሆኖ ይንቀሳቀሳል።
የገንዘብ አቅሙን ማሳደግ፣
3/ “ገንዘብ ካለህ በሰማይ መንገድ አለ” በሚለው ብሂለ አበውና
/ GYM
fitness makes you healthy man but money
GYM makes you powerful/ በሚለው ብሂለ ፈረንጅ እየታገዘ የገንዘብ አቅሙን ለማዳበርና
ፈርጣማ ክንድ እንዲኖረው ያለመታከት በመስራት ላይ ተጠምዶ የሚገኝ ሲሆን ይህንንም በመጻሕፍት፣ በመጽሔቶችና በሲዲ ሽያጭ እንዲሁም ሆቴሎችን በመክፈት፣ የንግድ ተቋማትን በመትከል፣ ህንጻ በመገንባት
ላይ መሰማራቱ የ20 ዓመታት እውነታ ነው። በዚህም የሚሊዮኖች ብር
ባለሃብት ለመሆን አስችሎታል። ይህ ከበጎ አድራጊዎችና ከአባላት መዋጮ የሚያግበሰብሰውን ሳይጨምር ነው። ባለሃብት መሆን ክፋት ባይኖርውም
የሰንበት ተማሪዎች ማኅበር ነኝ የሚል ማኅበር በዚህ ሁሉ የንግድ ዘርፍ ውስጥ መሰማራቱ ለስውር ዓላማው መሳካት የገንዘብን አስፈላጊነት
ከማመን የተነሳ ካልሆነ በስተቀር እወክለዋለሁ ከሚለው ስም አንጻር የቀደሙት ቅዱሳን በኢንቨስትመንት ላይ ተሰማርተው ነበር የሚል ጽሁፍ እስካሁን ቤተ ክርስቲያኒቱ
አላቆየችንም።