የኤልዛቤልን መንፈስ
ወደ እስራኤል
የሚጋብዝ አመራር
የዖምሪ ልጅ አክዓብ ከእርሱ
አስቀድሞ ከነበሩት ሁሉ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር
ፊት ክፉ ነገር አደረገ። የናባጥን
ልጅ የኢዮርብዓምን ሓጢአት እንደ
ቀላል ነገር ከመቁጠሩም በላይ የሲዶናውያንን
ንጉሥ የኤትበኣልን ልጅ ኤልዛቤልን
አገባ፤ ሄዶም በኣልን አመለከ፤ ሰገደለትም።
ሰማርያ ላይ በሠራውም የበኣል ቤተ
ጣዖት ለበኣል መሠዊያ አቆመለት።
ደግሞም የአሼራን ምስል ዐምድ በማቆም
ከእርሱ በፊት ከነበሩት የእስራኤል
ነገሥታት ይልቅ የእስራኤልን አምላክ
እግዚአብሔርን ለቁጣ የሚያነሣሣ
ድርጊት ፈጸመ።
1 ነገስት 16፡30-33 (አ.መ.ት)
በመጀመሪያ ማንኛውም አገልጋይ
መንፈሳዊ ሕይወቱን እንዴት መምራት
እንደሚገባው የራሱ የሆነ ሃላፊነት
አለበት። ይህንን ሃላፊነት ለመወጣት
ደግሞ የተለያዩ መሰናክሎች ሊያጋጥሙት
ይችላሉ። በተለያየ መንገድም በጣም
ወሳኝ የሆኑ የህይወት አማራጮች /ውሳኔዎች/
ውስጥም ሊገባ ይቻላል። እንግዲ እንደ
እኔ እምነት በነዚ ጊዜያቶች የአገልጋዩ
ለነገሮች ምላሽ የሚሰጥበት
መንገድ ወሳኝ ነው እላለሁ። ሁለት
መንገዶች አሉ… አንዱ መንገድ እንግዲ በተፈጠረው ወይም ውሳኔ
ባስፈለገው ነገር ላይ በማነጣጠር
/አእምሮው ወይም ስሜቱ/ በግል በሚለው
ውሳኔውን ማስተላለፍ ነው። ሌላው
ደግሞ ጉዳዩን ሳይሆን ቀና ብሎ ወደ
ጌታ በማየት የሱን ትክክለኛ ቃል በእምነት
ይዞ መንፈስ ቅዱስን ማዳመጥ። በሁለተኛው
መንገድ ለመራመድ እንግዲ የአገልጋዩ
ህይወት እለት እለት በቃሉ ሙላትና
በቃሉ በመኖር እንዲሁም ከመንፈስ
ቅዱስ ጋር ህብረት በማድረግ በጸሎት፣
በአምልኮ ከእግዚአብሔር አምላኩ
ጋር የጠለቀ ግንኙነት እለት እለት
ማዳበር ይኖርበታል። እነዚ ሲያነባቸው
የመጀመሪያ ትምህርቶች ናቸው ሊል
ይችላል ነገር ግን በእርግጥ ዛሬ ራሱን
ሊጠይቅ የምፈልገው ነገር፤ በእርግጥ
በቃሉ ምን ያህል እየኖረ
ነው። እርሱ በተመቸውና ዋጋ ባልከፈለበት
ብቻ ሳይሆን ምን ያህል ዋጋ እየከፈለ
ጌታ ጣል ያለውን ጥሏል? ዛሬ እኮ አንዳንድ
አሕዛቦች የአማኙን አንደበት አይተው
ጠጋ ሲሉት ህይወቱ ከነሱ የባሰ ሆኖ
ያገኙታል ደንብረው በዛው ይጠፋሉ።
እግዚአብሔር ዛሬ የሚለቅልህ
እውነት ልትኖርበት እንደምትችል
አውቆ እንድትኖርበት ነው። እንጂ
እንደፈሪሳዊ ሳትኖርበት ቃሉን ብቻ
እንድትናገር ወይም እንድትሰብክ
አይደለም። ያዘመን አልፏል። እግዚአብሔር ቃሉ በእምነት ከአገልጋዩ
ህይወት ጋር ተዋህዶ ለውጥ እንዲያመጣና
ንግግሩና ህይወቱ አንድ አይነት ምስክርነት
እንዲኖራቸው ይፈልጋ።
ዛሬ ስንቶች መድረክ ላይ በሚደንቅ
ትምህርታቸው ሚስቶቻቸውን አልጋዬን፣
ትዳሬን፣ ኑሮዬን እዚህ ላምጣ አሰኝተዋል
ምክንያቱም በቤታቸው ታሪካቸው ሌላ
ስለሆነ። በእነደዚህ አይነት ቸልተኛ
የክርስትና ሕይወት እየተመላለሱ
ጊዜን ማቃጠል ይብቃና እስኪ ዛሬ በቃሉ
እንዳትኖርበት፣ እንዳታድግ፣ በቦታህ
እንዳትገኝ (ያለቦታህ ቦታዬ እንድትል)
ባለህበት እንድትሄድ አዚም ያደርገውን
የህይወትህን አመራር ቀይር።
አዎ የአክዓብ
ሕይወት ሊያስተምረው ያለው ይሔው ነው በአመራር ደረጃም ቢሆን
በግል ህይወት ጤናማ ያልሆነ ውድጅትና
ጋብቻ የሚያመጣውን መዘዝ ይገልጻል።
አክዓብ እራሱንና ህዝቡን ቸልተኛ
በሆነ አመራሩ ምን ያህል
እንዳረከሰው እንመለከታለን።
እግዚአብሔር በአገልጋይ
ህይወት የማይፈልገው መንፈሳዊ ውድጅትና
ጋብቻ አለ። አንዳንዱ ከገንዘብ ጋር
ተጋብቷል አንዳንዱ ከዝናና ከስልጣን
ጋር ተጋብቷል ሌላው በራሱ በመመካት
ካለኔ ማን የተሻለ አለ ባይነት ገና
አለቀቀውም። እነዚህና ሌሎችም ብዙ
ሊጠቀሱ የሚችሉ እግዚአብሔር የማይፈልጋቸው
ጋብቻና ውድጅቶች ዛሬም በቤተክርስቲያን
መሪዎችና አገልጋዮች ህይወት ይስተዋላሉ።
በብሉይ ኪዳን አቤልን የገደለው
የቃየል ዘሮች ከእግዚአብሔር ፊት
ወጥተው በመሄዳቸው ከእግዚአብሔር
መገኘት ውጪ ያሉ ትውልዶች ናቸው ዘፍ 4፡16 ይመልከቱ። ዮሃንስ በመልእክቱ የክፉ ወገን
ብሏቸዋል 1ና ዮሃንስ 3፡6-12
በአንጻሩ ግን እግዚአብሔር በአቤል
ምትክ ልጅ ሰጠኝ ስትል ሴት ብላ ሔዋን
የሰየመችው አዳም 130 አመቱ የወለደው
የሴት ዘር ነው። የሄኖክና የኖሕ የዘር
ግንድ የአዳም ዘር ተብሎ ሲቆጠርም
የተጀመረው ከሴት እንጂ ከቃየል አይደለም።
እግዚአብሔር ልጆች ያሰኛቸውም እንደ
እግዚአብሔር ሀሳብ በመሄዳቸው በመታዘዘዛቸው
ነው ሔኖክ አካሔዱን ከእግዚአብሔር
ጋር ስላደረገ በ365 አመቱ እግዚአብሔር
ስለወሰደው አልተገኘም። ዘፍ 5፡23 ከውሃና ከመንፈስ የተወለደ
ዮሃ 3፡5 በልጁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ
የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት /የእግዚአብሔር
ልጅነትን/ ያገኛሉ።
“ከስጋ ተለይተን
ከጌታ ጋር መኖር እንደምንመርጥ እርግጠኛ
ሆኜ እናገራለሁ።” 2ኛ ቆሮ 5፡9
“ወንድም ነኝ” እያለ ከሚሴስን ወይም ከሚስገበገብ
ወይም ጣዖትን ከሚያመልክ ወይም ከሚሳደብ
ወይም ከሚሰክር ወይም ከሚቀማ ጋር
እንዳትተባበሩ ነው። 1ኛ ቆሮ 5፡11
ባጭሩ ወንድም ነኝ እያለ ነገር ግን በክርስቶስ ትምህርት የማይኖረውን ማለቱ ነው ይህ ደግሞ ገና ያልሞተው አዳም በውስጡ ስላለ (ለክርስቶስ የስጋውን ነገር ገና ያልገደለ) ባለበት መንፈሳዊ ደረጃ መግደል የሚገባውን የስጋ ሃሳብ በተረዳው መጠን ለመግደል ፈቃዱን ገና አልሰጠም፣ ቀድሞ የተጋባው መፋታት ያልፈለገው የሚያምረው ገና የሚያስጎመጀው በቲክና ሽንኩርት በህይወቱ አለ ይህ እለት እለት በክርስቶስ ትምህርት እየሄደ ራስ ወደ ሆነው ወደ ልጁ በሚያደርሰው ትምህርት ራሱን ካልሰራ ካልተለወጠ እየዋል እያደር ጥቂት እርሾ መሆኑ አይቀሬ ነው። በተለይ ደግሞ እንደዚህ አይነቱ በአመራር ቦታ ላይ ከሆነ ወይም የአገልግሎት ስፍራ ካገኘ እንደ አካብ በንዝህላልነት ወደ ቤተክርስቲያን የኤልዛቤልን መንፈስ ማስገቢያ ድለድይ መሆኑ አይገርምም።
እግዚአብሔር እስራኤሎችን
ሌላ ዜጋ እንዳያገቡ ሲከለክላቸው፤ ምክንያቱን በግልጽ አስቀምጦታል።
“ከእነርሱ ጋር ጋብቻ
አታድርግ ሴት ልጆችህን ለወንድ ልጆቻቸው
አትስጥ ወይም ለወንድ ልጆችህ ሴት
ልጆቻቸውን አታምጣ ምክንያቱም እኔን
ከመከተል ልጆችህን መልሰው ሌሎችን አማልክት እንዲያመልኩ
ስለሚያደርጉና ከዚህም የተነሳ የእግዚአብሔር
ቁጣ በላይ ነዶ ፈጥኖ ስለሚያጠፋህ
ነው።” ዘዳ
7፡3-4 / ዘጸ34፡15-17፣ ዕዝ 9፡12
በመካከላችሁ የዝሙት
እርኩሰት እንዳለ በእርግጥ ይወራል
እንዲህ ያለው እርኩሰት በአረማውያን
ዘንድ እንኳ የማይታይ ነው የአባቱን
ሚስት ያገባ ሰው አለና። ደግሞ ታብያችሗል!
ይልቅስ ሃዘን ተሰምቷችሁ ይህን ድርጊት
የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ልታስወግዱ
አይገባምን?
ይልና ዝቅ ብሎ ቁጥር 6 ላይ ደግሞ መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት
እርሾ ብዙውን ሊጥ እንደሚያቦካ አታውቁምን? 1ኛ ቆሮ 5፡1-6
እንግዲህ ግልጽ ነው፤ ጳውሎስ
በጊዜው የነበረውን ጠቀሰ እንጂ ዛሬ
ብዙ አይነት ቁርኝቶች አሉ እግዚአብሔር
የሚጸየፋቸው በእርሱ ስም ያልሆኑ
እንደ እርሱ ሃሳብና ፈቃድ ሳይሆን
ሰዎች እንደሚመቻቸው እነርሱ እንደፈቀዱት የሆነ ብዙ ህብረት፣
ጋብቻና ቁርኝት አለ። በዚህ
አይነቱ ሕብረት የሚበላሽ የአገልጋይ
ህይወት እንዳለው ሁሉ
በአገልጋዩ ህይወት ደግሞ እንደዚህ
ያለ ነገር ካለ ከትምክህት ይልቅ ንስሃ
በመግባት የእግዚአብሔርን የምህረት
ፊት ቶሎ ጊዜን ሳይባክን መፈለግ፣
መንገድን ማስተካከል አስተዋይነት
ነው።
እንግዲ የአካብ ህይወት
ከሚያስተምረን
1. የናባጥ ልጅ የኢዮርብአምን
ሃጢያት እንደቀላል መቁጠሩ
የአክዓብ አባት ዖምሪ ራሱ በኢዮርብዓም መንገድ
መሄድ ምንም ያልመሰለው ሰው ነው።
እንደውም ከታምኒን ጋር በነበረው
ወደ አራት አመት የፈጀ የስልጣን ጦርነት
እርዳታ ለማግኘት ይመስላል ከኤልዛቤል
አባት ከኤትበኣል ጋር ተወዳጀ። ከዛም
አልፎ ልጁን አካብን ከኤልዛቤል ጋር
አጋባ።
እዚ ላይ ልብ ልንለው የሚገባ
ነገር አለ አገልጋይ በህይወቱ በተለያየ
ምክንያት፣ ጥቅማጥቅሞች፣ ሕይወቱን፣
ከአገልግሎቱ፣ ከእለት ተእለት ጉርሱና
ምቾት ወይም ድሎት ጋር በፍጹም ማገናኘት የለበትም። ምክንያቱም
አንዳንድ አገልጋዮች ጸጋቸውን ወይም
አገልግሎታቸውን ለግል ምድራዊ ኑሮአቸው
መጠቀሚያ ሲያደርጉት
እንደዚሁም አንዳንድ
መሪዎች በተመሳሳይ ሁኔታ ለአንዳንድ
አላስፈላጊ ስራቸው የሚተባበሩአቸውን
መወዳጀታቸው መጨረሻው ወደየት እንደሚያመራ ግልጽ ነውና። አክዓብ ኢዩ
እንዲቀባ ትእዛዝ ከእግዚአብሔር
ከወጣ በሗላ እንኳ ሁለት ታላላቅ ጦርነቶችን
እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ያውቅ
ዘንድ ድልን አግኝቷል። ይህ ማለት
አክዓብ በትክክለኛ መንገድ ላይ ነው
ማለት አይደለም ከክፋቱ ይመለስ ዘንድ
የእግዚአብሔር ምህረት በዝቶለት
እንጂ። ዛሬም በእነደዚህ አይነት
በባከነ ጊዜአቸው ጳውሎስ ለቆሮንጦስ
እንደጻፈላቸው በሐዘን ስህተታቸውን
ማረም ሲገባቸው የሚታበዩ ለንስሃ
የተሰጣቸውን ድል ለእውነተኛነታቸው
እንደ ማስረጃ የሚሰብኩ አልታጡም። የሰዉ ቁጥር በቤተክርስቲያን
ውስጥ ሲመናመን ከብዛት ጥራት በርከት
ሲል ወይም የጠፉ በጎች ሲመለሱ ካለኛ
ማን አለ ማለት ከንቱነት ነው። ማንን
ነው የምናታልለው? ራሳችንን? ከእኛ
የሆነ አንዳች የለም ሁሉም ከእርሱ
ነውና ይልቅስ ስለምህረቱ እግዚአብሔርን
እያመሰገኑ መንገድን ማስተካከል
እና ይበልጥ እግዚአብሔርን የምናውቅበተን
መንገደ መፈለግ መልካም ነው። ትክክለኛውና እግዚአብሔርም የሚሻው ይኸው ነው።
“አሕዛብ ፈቅደው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣
በስጋዊ ምኞት፣ በስካር፣ በጭፈራ፣
ያለ ልክ በመጠጣት፣ በአጸያፊ የጣዖት
አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው
ዘመን ይበቃል።”
1ኛጴጥሮስ 4፡3 አዎ ይበቃል!!
አርሱ ንጹህ እንደሆነ ራስህን አንጻ!
1ኛጴጥሮስ 4፡3 አዎ ይበቃል!!
አርሱ ንጹህ እንደሆነ ራስህን አንጻ!
“በእርሱ የሚኖር ሃጢያትን
አያደርግም፤ ሃጢያት
የሚያደርግ ግን እርሱን አላየውም
ወይም አላወቀውም። ልጆች ሆይ ማንም
እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ እርሱ ጻድቅ
እንደሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ
ነው። ዝቅ ብሎ ቁጥር 10 መጨረሻ ላይ ጽድቅን
የማያደርግ፣ ወንድሙንም የማይወድ
ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። ከመጀመሪያ
የሰማችሗት፣ እርስ በርሳችን
ልንዋደድ ይገባል የምትለዋ
መልእክት ይህች ናትና። የክፉው ወገን
ሆኖ ወንድሙን እንደገደለው እንደ ቃየን አትሁኑ።” 1ኛ ዮሃን 3፡6-12
በትክክለኛው መንገድ
ከእግዚአብሔር ጋር መወዳጀት በምንም
ውስጥ ቢሆን ያዋጣል። በሰው
ከመታመን በእግዚአብሔር መታመን
ይሻላልና። እንደውም አንድ ነገር
ትዝ አለኝ እዚጋ የመጽሃፍ ቅዱስ መካከለኛው
ምእራፍ 118 ሲሆን መካከለኛው ጥቅስ ደግሞ
118 ቁጥር 9 ነው። “በገዦች ተስፋ ከማድረግ
ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።”
መዝ.118፡9 ስለዚህ ውድጅታቸን ከእግዚአብሔር
ጋር ጋብቻችንም ከክርስቶስ ጋር ሊሆን
ይገባል።
2. አክዓብ ዔልዛቤልን
አገባ
አክዓብ ኤልዛቤልን ያገባው በእስራዔል ላይ ከመንገሡ በፊት ነው። ስለዚህም ከመንገሱ በፊት በራሱ ላይ ከነገሠ በሗላ ደግሞ በሕዝቡ ላይ ለከፍተኛ ጥፋት ምክንያት ሆኗል።
* አክዓብ ኤልዛቤልን ሲያገባ አባቷ የበኣል ጣዖት ካህን የነበረ ሰው መሆኑን ያውቅ ነበር።
* የጣዖት አምልኮዋን በግልጽ የምታደርግ ናት፣ በግልጽ የምታስፋፋም ናት።
* ከእስራኤል ወገን አይደለችም።
አክኣብ እንግዲ ኤልዛቤልን ሲያገባ ይሄን ሁሉ ነገር እያወቀ ነበር። ይህ ደግሞ አክኣብ ለእግዚአብሔር ትእዛዝ ቸልተኛ መሆኑን ያሳያል። ከቸልተኝነቱም የተነሳ ልክ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው ኤልዛቤልን አገባ፣ ለበኣል ሰገደለት፣ እንደውም ሠማርያ ላይ ለበኣል ቤተ ጣዖት ሰራ፣ መሰዊያም አቆመለት በዚ ብቻም አላቆመም የአሼራንም ምስል አምድ አቆመ። እንግዲህ አክአብ ጠቅላላ የኤልዛቤል መንፈስ ተቆጣጥሮታል። የጋብቻውም ፍሬ እንግዲ ይህን ይመስላል።
ብዙ ነገሮችን ዛሬ አገልጋዮች እያወቁ ይጋባሉ የራሱን ሃሳብ ሲገነባ እየታየ አብሮ ይገነባል፣ ወነንድሙን በጥላቻ ወይም በቅናት ሲያጥላላ እንደ ኤሊያስ እውነቱን ሲናገር እርሱ ስለኔ መልካም አይናገርም በቤተክርስቲያን ላይ ያሟርታል በሚል ጥላቻ የሚያናፍሰውን እውነት እንዳልሆነ እያወቀ አብሮ የሚያናፍስና የሚያወግዝ፣ ለምን ብሎ የማይጠይቅ ወይም በመካከል ሰላምን ለማምጣት የማይጥር እውነቱን ለማወቅ ፈጽሞ የማይጥር ነገሮችን ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር የማይመረምር ወንድሙን በክርስቶስ ሳይሆን እያወቀ በተሳሳተው በዛ ሰው የሚመለከት የቸልተኛ አገልጋይን ሕይወትን ያሳየናል። በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ለሚጸየፈው ህብረት፣ ጋብቻ ወይም ቁርኝ እራሱን አሳልፎ ይሰጣል።
አክዓብ ኤልዛቤልን ያገባው በእስራዔል ላይ ከመንገሡ በፊት ነው። ስለዚህም ከመንገሱ በፊት በራሱ ላይ ከነገሠ በሗላ ደግሞ በሕዝቡ ላይ ለከፍተኛ ጥፋት ምክንያት ሆኗል።
* አክዓብ ኤልዛቤልን ሲያገባ አባቷ የበኣል ጣዖት ካህን የነበረ ሰው መሆኑን ያውቅ ነበር።
* የጣዖት አምልኮዋን በግልጽ የምታደርግ ናት፣ በግልጽ የምታስፋፋም ናት።
* ከእስራኤል ወገን አይደለችም።
አክኣብ እንግዲ ኤልዛቤልን ሲያገባ ይሄን ሁሉ ነገር እያወቀ ነበር። ይህ ደግሞ አክኣብ ለእግዚአብሔር ትእዛዝ ቸልተኛ መሆኑን ያሳያል። ከቸልተኝነቱም የተነሳ ልክ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው ኤልዛቤልን አገባ፣ ለበኣል ሰገደለት፣ እንደውም ሠማርያ ላይ ለበኣል ቤተ ጣዖት ሰራ፣ መሰዊያም አቆመለት በዚ ብቻም አላቆመም የአሼራንም ምስል አምድ አቆመ። እንግዲህ አክአብ ጠቅላላ የኤልዛቤል መንፈስ ተቆጣጥሮታል። የጋብቻውም ፍሬ እንግዲ ይህን ይመስላል።
ብዙ ነገሮችን ዛሬ አገልጋዮች እያወቁ ይጋባሉ የራሱን ሃሳብ ሲገነባ እየታየ አብሮ ይገነባል፣ ወነንድሙን በጥላቻ ወይም በቅናት ሲያጥላላ እንደ ኤሊያስ እውነቱን ሲናገር እርሱ ስለኔ መልካም አይናገርም በቤተክርስቲያን ላይ ያሟርታል በሚል ጥላቻ የሚያናፍሰውን እውነት እንዳልሆነ እያወቀ አብሮ የሚያናፍስና የሚያወግዝ፣ ለምን ብሎ የማይጠይቅ ወይም በመካከል ሰላምን ለማምጣት የማይጥር እውነቱን ለማወቅ ፈጽሞ የማይጥር ነገሮችን ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር የማይመረምር ወንድሙን በክርስቶስ ሳይሆን እያወቀ በተሳሳተው በዛ ሰው የሚመለከት የቸልተኛ አገልጋይን ሕይወትን ያሳየናል። በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር ለሚጸየፈው ህብረት፣ ጋብቻ ወይም ቁርኝ እራሱን አሳልፎ ይሰጣል።
አንድ ወንድም ሲያስተምር ምን
አለ ክርስትና ስሌት ነው የሚጀምረውም
ከመቀነስ ነው ትክክል ነው።
በመጀመሪያ የኔ የምትለውን ነገር
ሁሉ ቀንሰህ መጨረስ አለብህ አለዛ
እየዋለ እያደር ተጽእኖ እያመጣ ወደ አሳዛኝ መንገድ መውሰዱ አይቀርም።
አክአብ የራሱን ነገር ትቶ ቢሆን ኖሮ
ምን ያህል ታሪኩ ሊቀየር እንደሚችል
መገመት አያዳግትም።
”ማንኛውም የዝሙት ወይም የርኩሰት ወይም የሥሥት ነገር ከቶ በመካከላችሁ አይነሳ ይህ ቅዱስ ለሆነው ለእግዚአብሔር ሕዝብ አይገባምና” ኤፌ. 5፡3
”ማንኛውም የዝሙት ወይም የርኩሰት ወይም የሥሥት ነገር ከቶ በመካከላችሁ አይነሳ ይህ ቅዱስ ለሆነው ለእግዚአብሔር ሕዝብ አይገባምና” ኤፌ. 5፡3
እነዚህ ከላይ በጳውሎስ የተጠቀሱት በመካከላችሁ አይነሳ ሲል ስለማይገባን እንደሆነ ተናግሮታል ስለዚህ እነዚ ነገሮች መልካቸውን እየቀያየሩ በጥቂትም ይሁን በስፋት ስናይ አንባቢው ልብ ሊል
ይገባዋል
ወዴት እየሄደ እንደሆነ።
3. ስልጣኑን አሳልፎ
የሰጠ ነው።
ኤልዛቤል በእርሱ ስልጣን ትፈልጥና ትቆርጥ ያሻትን ታደርግ ስለነበር ናባልን፣ ነቢያትን አስገድላለች። ኤልያስን አስፈራርታ ከቦታው እንዲሸሽ አድርጋለች። ለዚህ የእግዚአብሔር ቃል “በሚስቱ በመመራት እራሱን ለሃጢያት የሸጠ እንደ አክኣብ ያለ የለም” በማለት ገልጾታል።
ኤልዛቤል በእርሱ ስልጣን ትፈልጥና ትቆርጥ ያሻትን ታደርግ ስለነበር ናባልን፣ ነቢያትን አስገድላለች። ኤልያስን አስፈራርታ ከቦታው እንዲሸሽ አድርጋለች። ለዚህ የእግዚአብሔር ቃል “በሚስቱ በመመራት እራሱን ለሃጢያት የሸጠ እንደ አክኣብ ያለ የለም” በማለት ገልጾታል።
አገልጋዮች በሚገባ አገልግሎታቸውን
እንዳይወጡ፣ በትክክል በቦታቸው
እንደሚገባ እንዳይቆሙ፣ እግዚአብሔር
በሰጣቸው ጸጋ እንዳይቆሙ፣ መንፈሳዊ
ቦታቸውን እስከ ማስለቀቅ ድረስ በአገልጋዩ
ሕይወትና በቤተክርስቲያን
አገልግሎት ስልጣኑን ለክፉ ጋብቻ
አሳልፎ በሰጠ ከመንፈስ ቅዱስ ይልቅ
በስሜቱ፣ በስጋ ፍላጎቱ ተጽእኖ በተያዘ
መሪ አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው።
እዚ ላይ መሪ ስል በቤተክርስቲያን
የበላይ የአመራር አካሉን ሲሆን፣
በአገልጋዩ ሕይወት ደግሞ ሕይወቱን
በጥንቃቄ የመምራት ሃላፊነት ያለበት
እራሱን አገልጋዩን ነው። ምንጊዜም
ያለ ቦታው የቆመ ነገር ካለ በቦታው
መቆም ያለበት ላይ ችግር መፍጠሩ የማይቀር
ነው። ለምሳሌ ንህምያ ወደ ባቢሎ ተመልሶ
በነበረበት ወቅት ካህኑ ኤልያሴብ ከጦቢያ ጋር የጠበቀ ግንኙነት
(የጋብቻ ቁርኝት) ስለነበረው በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ
ለጦቢያ አንድ ክፍል መኖሪያ
በመስጠቱ፤ ሃላፊነቱን አጉድሏል
ሌሎችም እንደሚገባ ሃላፊነታቸውን
እንዳይወጡ እንቅፋት ሆኗል። ሌዋውያኑ
የተመደበው ድርሻ ስላልተሰጣቸው
ሃላፊነታቸውን መወጣት ስላልቻሉ
ወደ የእርስታቸው እንደሄዱ የንህምያ
የመጨረሻ ተሃድሶ እርምጃ ላይ እናገኘዋለን ንህምያ 13
እዚጋ በደንብ እንድታስተውለው
የሚያስፈልግ ነገር አለ። እግዚአብሔር
እንዲህ እንድታደርግ እፈልጋለሁ
ብሎ ልታደርገው የሚገባህን ነግሮህ
ስልጣንም ሰጥቶህ ሳለ፣ ነገር ግን
ራስህን፣ ወዳጆችህን፣ አብረውህ
የሚያገለግሉ አገልጋዮችን፣ ያገርህ
ልጆችን፣ ወይም በአገልግሎታቸው
በጣም ይጠቅማሉ ብለህ የምትታምንባቸው
ሰዎች፣ ታላላቅ አገልጋዮች ብለህ
እንኳ የምታከብራቸው፣ አካባቢህና
ጥቅማጥቅሞችህ ለሚሉህ
ነገር፤ ፈጽመህ ልታደርግ ከተቀበልከው
ተግባር ወደሗላ ማለትም ሆነ ለተግባርህ
መወጫ የተሰጠህንም ስልጣን ለሌላ
አሳልፈህ መስጠት ፈጽሞ እንደሌለብህ
ልታስተውል ግድ ነው። ምክንያቱም
የተቀበልከውን አደራ ከመወጣት ወደሗላ
ባልክ ጊዜ ስልጣንህን ወደሗላ ላስባለህ
ነገር አሳልፈህ እየሰጠህ ነው። ስለዚህ
እንደ ኤልዛቤል እየዋለ እያደረ ባንተ
ስልጣን እርሱ ማስተማር የምታውቀውን
ቃል እየጠቀሰ እርሱ መስበክ ይጀምራል።
ጨርሶም ይቆጣጠርሃል። ከዛ ጌታ ማለት
የፈለገው ሌላ አንተ የምትለው ሌላ
ይሆንና በሃሰት ትምህርት የአገልጋዩን
ጊዜ ከማባከንህም በላይ በሰአቱና
በጊዜው መድረስ ወደሚገባው እንዳይደርስ
መሰራት የሚገባው እንዳይሰራ እንቅፋት
ትሆናለህ። የሃሰት ትምህርት ከጌታ
የሚያርቅ ፍቅር እንድትቀዘቅዝ የሚያደርግ
ነው። እንግዲ አሰራሩ ሊለያይ ይችላል።
ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ቃል አካፋይ
ብትሆን ጌታ በቃሉ ልክ እንደገለጠልህ
ሳትጨምርና ሳትቀንስ ግራና ቀኝ ሳትል ማንንም ለማስደሰት ማንንም
ባገኘኸው አጋጣሚ ለመጥረብ ሳይሆን
ልክ እንደተቀበልከው እንደዛው የማስተላለፍ
ግዴታ አለብህ ያንን የመቀየር ምንም
ስልጣን የለህም። ነገር
ግን ከቀየርከው፣ ከላይ
እንደተጠቀሰው የምታደርግ ከሆንክ
የተሰጠህን ተግባር ቸል ብለሃል ስልጣንህንም
አሳልፈህ ሰጥተሃል ማለት ነው።
መሪም ቢሆን አገልጋይ እንደዛው ነው። ለጓደኞቹ
የሚመራ፣ በጓደኞቹ የሚመራ፣ የጊዜያዊ
ኑሮውን የሚያስቀድም፣ ባጠቃላይ
በስጋና በምድራዊ ነገር የሚመራ ከሆነ፣
ዋጋ ከፍሎ ሃላፊነቱን ለመወጣት በተናገረው
በቃሉ የማይገኝ፣ የማይታመን
ከራሱ ይልቅ ለሌሎች የማይማልድ ራሱን
ዝቅ አድርጎ ተምሳሌነቱን የማይገልጥ፤
በዛም ደግሞ ታዛዥ የሖነን
ጉባኤ የማያተርፍ፣ እንደውም አርሱ
የሚለውን ስለሚቀበሉት ብቻ እውር
አውርን ቢመራው እንደሚሉ ብጤዎቹን ይዞ የሚሮጥ ከሆነ። ጉባዔውም
በአመጽ የተሞላ የተከፋፈለ እርስ
በእርስ መግባባት ከቶ የሌለበት ባለህበት
ሂድ ብቻ ሳይሆን እለት እለት የሗልዮሽ
መሄድ መጀመሩና በሃሳቦች መካከል
ማነከሱ አይቀርም።
ይህን ደግሞ መለየት ምንም አያዳግትም ምክንያቱም በህይወቱ፣ በአኗኗሩ በፍሬው የተገለጠ ነው።
4. በናቡቴ ላይ ግፍን አስፈጸመ
የእስራኤል ንጉስ ስልጣን
የራሱ የሆነ የተወሰነ
የኪዳን ህግ ስለነበረው
እርስቱን በጉልበቱ መቀማት አይችልም
ስለዚህም ነው ያግባባው። ዘዳ. 17፡14-20፣
1ኛ ሳሙ 10፡25 ይመልከቱ ሳሙኤል በመሰነባበቻ
ንግግሩ ላይ እንዲህ ብሎ
ነበር… ፡ “እነሆ
በፊታችሁ ቆሜ አለሁ በእግዘዚአብሔርና
እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ የማንን
በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ?
ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሰራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆን
ከማን እጅስ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ
አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችሗለሁ” 1ኛ ሳሙ 12፡3
አክኣብም ይህን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነበር በብስጭት ወደቤቱ የገባው። ኤልዛቤል ግን ለእስራኤል ስርኣትና ደንብ ባእድ ስለሆነች ግድም ስለማይሰጣት እንደውም ተቃራኒ ስለሆነች። ንግስናውን አጣጥላ ጭካኔ በተሞላው አነጋገርና ድርጊት ሃሳቡን ስታስፈጽም ይታያል።
አክኣብም ይህን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነበር በብስጭት ወደቤቱ የገባው። ኤልዛቤል ግን ለእስራኤል ስርኣትና ደንብ ባእድ ስለሆነች ግድም ስለማይሰጣት እንደውም ተቃራኒ ስለሆነች። ንግስናውን አጣጥላ ጭካኔ በተሞላው አነጋገርና ድርጊት ሃሳቡን ስታስፈጽም ይታያል።
እንግዲህ እንደ አክአብ ያሉ ቸልተኛ
መሪዎች፡ እንደ እግዚአብሔር ሃሳብ ባልሆነው ጋብቻቸው አገልጋዮችን
ከእርስታቸው የማስለቀቅ ተልእኮ
ያስፈጽማሉ። ይኸውም እግዚአብሔር
በተሰጠህ ጸጋ እንዳትቆም
በተለያየ መንገድ ውጊያ በመክፈትና
በማስከፈት ብቃትህን ከጌታ
የተሰጠህ ቃል ሊሆን ይችላል፣ ወይም
ዝማሬ ሊሆን ይችላል፣ ትንቢት ይሆናል
ሌላም ቢሆን ያንን ማዳፈን
ይሞክራል። እግዚአብሔር በውስጥህ
ያስቀመጠውን ጸጋ እጅ እየጫነ ማቀጣጠል
ሲገባው ነገር ግን ትክክለኛውን አገልጋይ
በትክክለኛው ቦታ እንዳይቆም በተለያየ
መንገድ ይዋጋዋል። ቦታውን ለማሰለቀቅ
ቢችል በቀጥታ ባለው ስልጣን በመጠቀም
ካልቻለም ደግሞ ክስን በመመስረት
እንደርሱ የመሰሉትን ሰውን በክርስቶስ
ሳይሆን በእርሱ እይታ የሚያዩትን
አመለካከታቸውን እያቆሸሸ በመካከል
መከፋፈል እንዲኖር እያደረገ ትክክለኛው
ስራ በትክክለኛው ሰአት እንዳይስራ
ስውር ተልእኮ በመፈጸም ቤተክርስቲያን
በሰአቱና በጊዜው መቆም የሚገባት
ቦታላይ እንዳትደርስ ያላሰለሰ ጥረት
ያደርጋል። አገልጋዩ ከእግዚአብሔር
በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የተቀበለውን
እውነት ሲያስቀምጥ እንደነ አክአብ
ያሉ መሪዎች ስለማይመቻቸው። አንተ
እስራኤል የምታውክ ማለታቸው አይቀሬ
ነው። ስምን ማጥፋት ጸጋን አለመቀበል
ነው። በሌላ በኩል ደግሞ
የእግዚአብሔር መንፈስ ከኛ አልፎ
እንዴት ወደ አንተ መጣ ብሎ እንደነ
ሴዴቂያስ በጥፊ የሚማታ ከዛም አልፎ
ጥቅስን በመደርደር የተናገርከውን
መልእክት ያለኔ ማን ያውቃል ከእኔ
በላይ ላሳር በሚል ትምክህት ስራ ማስፈታት
ነው።
መመካታችሁ መልካም አይደለም ጥቂት እርሾ ብዙውን ሊጥ እንደሚያቦካው አታውቁም?
1ኛ ቆሮ 5፡6
መመካታችሁ መልካም አይደለም ጥቂት እርሾ ብዙውን ሊጥ እንደሚያቦካው አታውቁም?
1ኛ ቆሮ 5፡6
ስለዚህም አገልጋይ ነኝ
እየተባለ የሚያስፈጽመው ተልእኮ
ግን በተቆጣጠረው መንፈስ በፈጸመው
ጋብቻ ተጽእኖ ስር ወድቆ የጨለማን
ስራ በስውር ያስፈጽማል።
ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ህብረት አለው 2ኛ ቆሮ 6፡14ለ
ብርሃን ከጨለማ ጋር ምን ህብረት አለው 2ኛ ቆሮ 6፡14ለ
እንግዲህ በጣም በጥቂቱ
ማለት ይቻላል ከአክአብ ሕይወት እንዴት
ወደ ጥፋት እነደገባ አሰራሩን ካየንና
ለእኛ ደግሞ እንዴት ትምህርት እንደሆነን
ከተረዳን፣ ዛሬ በቤተክርስቲያን
በረቀቀ መልኩ እንዴት እየሰራ እንዳለ
ካየን እስኪ ደግሞ የእግዚአብሔርን
ትእግስትና ይቅርታ እንዲሁም ምህረት
እና ምላሹን ከዚሁ ከአካብ ህይወት
ትንሽ እንመልከት።
አዎ እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ
ላይ በሚደርሰው ግፍና
በደል እጅግ ይቆጣል አጸፋወንም መመለሱ
አይቀሬ ነው። ቢሆንም ደግሞ እግዚአብሔር
እንደሰው ስላልሆነ አይቸኩልም እንደዚሁም
አይጨክንም የምህረት ልብ ስላለው
ከስህተታችን እንማር ከሆነ ይራራል።
እግዚአብሔርም በአክአብ
ቦታ ይነግስ ዘንድ ኢዩን እንዲቀባ
ኤልያስን ላከ። እግዚአብሔር
ይህን የተናገረው በ1ኛ ነገስት 19፡16
ላይ ነው። ከዚህ በሗላ ግን በምእራፍ
20 ቁጥር 13/ለ ላይ እግዚአብሔር ለአክአብ
እንዲህ አለው “ ይህን ብዙ
ሰራዊት ታያለህን? ዛሬ በእጅህ አሳልፌ
እሰጥሃለሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር
መሆኔን ታውቃለህ ” አለው።
እንግዲህ እግዚአብሔር
አክአብ ቢማር ቢመለስ እኔን ቢታዘዝ
ብሎ ሲራራለት ድል ሲሰጠው እናያለን።
ከዚህ በሗላ ነቢዩ ወደ እክአብ መጥቶ
በሚመጣው የጸደይ ወራት የሶርያው
ንጉስ ቤንሃዳድ ተመልሶ ሊዋጋ እንደሚመጣ ነግሮት
እንዲበረታና ምን ማድረግ እናለበት
እንዲያውቅ ነገረው። እዚህ ላይ የጦርነቱን
ድል የሰጠው እግዚአብሔር ነው ስለዚህ
እንዴት ተዋግቶ እንደሚያሸንፍ አይደለም
መናገር የፈለገው ነገር ግን እንዴት
የእግዚአብሔርን ፊት ማጝኘት እንደሚችል
ነው ምህረቱን ቸርነቱን ታዳጊነቱን
እንዴት ማግኘት እነደሚችል እንጂ
በራሱ ከመመካት እንዲወጣ የእርሱ
ትምክህት ከንቱ ስለሆነ እግዚአብሔርን
እንዲያውቅ ነበር የዚህ ስሙ ያልተጠየቀሰ
ነቢይ መልእክት። ምን ማለት ነው፣
እንግዲህ ዛሬም በአዲሱ ኪዳን ዘመን
ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን አሳራሩን
የዛሬውን ሃሳቡን እቅዱን ታውቅ ዘንድ
ይህንንም አውቃ መንገዷን በጌታ ፈቃድ
በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ትወጣና ትገባ
ዘንድ እንድትማር እድል ሲሰጣት፣
ነገር ግን ለዛ ቀድመው ሲያዘግሙበት
ለነበረው መንገዳቸው እግዚአብሔር
እንዲጥሉት ደጋግሞ ለሚነግራቸው
አካሄዳቸው እግዚአብሔርን ስለታዘዙ
እንደማስረጃ ወይም ትክክለኛ ስለሆኑ
ያን ድል እንዳገኙ ስለሚሰብኩ ከዚህ
ተረት ተረት ውጡ ነው መልእክቱ።
ምክንያቱም በተደጋጋሚ
እድሉን ቢያገኙም ተመልሰው እዚያው
ሊጥሉት ያቃታቸው ስርአታቸው ውስጥ
ይገኛሉ። አካብን ተመልከቱ እግዚአብሔር
መንገዱን ስላስተካከለ ሳይሆን ነገር
ግን ሶርያውያን እግዚአብሔርን
የኮረብታ እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም
በማለታቸው ያን ስፍር ቁጥር የሌለውን
ሰራዊት እንደ ሁለት የፍየል
መንጋ በሚያክለው የእስራኤል ሰራዊት
ፊት በታተነው። ነገር ግን እዚህ ላይ
አሁንም አክአብ በራሱ ውል እርሱ የመሰለውን
ውል ተፈራርሞ ካለእግዚአብሔር ፈቃድ
ቤንሃዳድን ለቀቀው። በዚህም ምክንያት
እግዚአብሔር በቤንሃዳድ ገመድ አንተ
በህዝቡም ገመድ ህዝብህ ይገባል ብሎ
መልእክት ላከበት።
እንግዲህ ዛሬ ለኛ ትምህርት
የሚሆነን እግዚአብሔር በሚሰጠን
ምህረት ተጠቅመን መንገዳችንን እንድናስተካክል
የሚሰጡንን ድሎች ለትምክህት ከምንጠቀምባቸው
ይበልጥ የእግዚአብሔርን ማንነት
አውቀን እንዴት እንድንራመድ አውቀን
እርሱን እየታዘዙ መሔዱ ከቁጣው ያድነናል
አልያ እነደ አክአብ አልለቅም ብለን
የሙጥኝ ካልን…
በቁጣው
እግዚአብሔር እንዲህ አለ…”ውሾች
የናቡቴን ደም በላሱበት ቦታ የአንተንም
ደም እንዲሁ ውሾች ይልሱታል!” ብሎ በአገልጋዩ አንደበት
ሲናገር የአክአብ ምላሽ ጠላቴ ሆይ
አገኘኸኝ ነበር ኤልያስም መልሶ በእግዚአብሔር
ፊት የተጠላውን ነገር ለማድረግ ራስህን
ሸጠሃልና አዎን አግኝቼሃለሁ አለው።
ዘሩንም ፈጽሞ እንደሚያጠፋ ወንድ
ልጆቹን ሁሉ እንደሚያጠፋ እንዲሁም
ከኣክአብ ጋር ወግኖ የተሰለፈውን
ሁሉ በከተማም ይሁን በገጠር ያሉትን
ሁሉ እንደሚያጠፋ ይናገራል 1ኛ ነገስት
21፡19-24 ይመልከቱ
አዎ ዛሬ እውነተኛ ከእግዚአብሔር
ዘንድ የሆነውን የጊዜውን ቃል ስትናገር
እንደ አክአብ ያሉ መሪዎች
ወይም አገልጋዮች በጠላትነት፣ በተቃዋሚነት
ማየታቸው አይቀርም የእግዚአብሔርን
መርህ ስታስቀምጥላቸው ለዘሩት ዘር
አጸፋውን መቀበላቸው እንደማይቀር
ስትናገር ሟርተኛ ማለታቸው አይቀርም።
ቁም ነገሩ ግን ዛሬ በአንደበታቸው
አይናገሩት እንጂ በልባቸው እንደ
አክአብ አገኘኸኝ ማለታቸው አይቀርም።
ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ
ይለናል…
በምትፈርዱበትም ዐይነት ይፈረባችሗል፤ በምትሰፍሩበትም
መስፈሪያ ይሰፍርላችሗል። ማቴዎስ 7፡2
እንግዲ እውነትን፣ ፍቅርን፣
በጉባኤው ብትዘራ እንደዛው ፍቅርን
ታጭዳለህ የወንድሞችህን ጸጋ ብታከብር
እንደዚሁ፣ እምነትን ብትዘራ፣ ሰዎችን
ብትቀበል፣ መልካሙን ሁሉ ብተታደርግ፣
ላንተም እንደዛው ይሆንልሃል፣ ነገር
ግን በስልጣንህ ለመቆየት ባልተሰጠህ
ጸጋ ተለይተህ ለመስራት እየሞከርክ
ዘመንህን ሁሉ በተከፋፈለ ጉባኤ ጊዜህን
እያቃጠልክ ለጉባኤውም ጠንቅ ሆነህ
ሳለህ መልሰህ ወቀሳ ለጉባኤው ብታሰማ
ከንቱ ውዳሴ ነው የሚሆነው፤ ይልቅስ
እለት እለት የምትዘራውን አስብ ባንድ
ወቅት ሳሙኤል መሰነባበቻ ንግግሩ
ላይ እንዳለው በጉባኤ መካከል ማለት
ከመቻል ያለፈ ህይወት ሊኖርህ ይገባል።
ባትቀበል አንተንም የሚቀበልህ እንደዛው
ይጠፋል ብትጠላ አንተም የምታጭደው
ያንንኑ ነው። ሰዎችን እየከፋፈልክ
ለመቆየት ብትታገል አንዴም ሳታርፍ
ሁል ጊዜ በተከፋፈለ ጉባኤ
መካከል ተገዙ፣ ተቀበሉ፣ እመኑ፣
በዚ አሰልቺ ትምህርትህ ጉባኤው ሲጎድል
ከብዛት ጥራት እያልክ ምንም ለውጥ
ሊያመጣ፣ የማንንም ህይወት ሊሰራ
በማይችል ከንቱ ዲስኩር የራስህንም
የጉባኤውንም ጊዜ ስታባክን ትኖራለህ።
ይልቁንም እምትዘራውን አስተውል።
እስኪ ወደ አካብ እንመለስና የነቢዩን
የኤሊያስን ያልተመቻመቸ መልእክት
ሲሰማ አክአብ ልብሱን ቀዶ ማቅ ለብሶ
ጾመ በማቅ ላይ ተኛ በሐዘን ኩርምት
ብሎም ይሄድ ነበር።
1ኛ ነገሰት 21፡27
1ኛ ነገሰት 21፡27
እዚ ላይ የምንመለከተው
አክአብ በዘመኑ በነበረው መረዳት
እግዚአብሔር ይቅር እንዲለው እራሱን
በእግዚአብሔር ፊት አዋረደ እግዚአብሔርም
በምህረቱ ቅጣቱን ከሱ ዘምን ወደ ልጁ
ዘመን አዛወረለት። በእስራኤልም
ለሶስት አመት ምንም አይነት ጦርነተ አለልነበረም። ነገር
ግን በሶስተኛው አመት አክአብ ሬማት
ላይ ለመዝመት አሰበ በእርግጥ ሬማት
ከሙሴ ዘመን ጀምሮ የእስራኤላውያን ከተማ ነበረች ለማስመለስ
መሞከሩ መልካም ቢመስልም ነገር ግን
በእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም
የወጣው ስለዚህም ነብዩ የነገረውን
ሳይሆን ለእራሱ ፍላጎት በንግግራቸው
የተስማሙትን በዙሪያው የሰበሰባቸውን
ሀሰተኛ ነቢያቶች ሰምቶ ወደ ሞቱ ሲቸኩል
እናያለን።
ዛሬ በቤተክርስቲያን እንደ
አክአብ የግሉን ጥቅም ማስጠበቅ
ወይም ደግሞ የአገልግሎት ቦታውን
በራሱ ሃሳብ እና እቅድ መያዝ እና በዛም
መቆየት በሚፈልጉ ለዚያም ደግሞ የራሳቸው
የሆነ እነርሱን በሚመስል አገልጋይ
የተከበቡና ከሃሳባቸውና ከራሳቸው
እቅድ ወይም በዙሪያቸው ከከበቡአቸው
የእነርሱ ሃሳብንና እቅድን ለማስፈጸም
ከሚተጉ እንጂ እግዚአብሔር በእውነት
ዛሬ ምን እንደሚፈልግ በትክክል ለማረጋገጥ
ግድ በማይላቸው ቸልተኛ አገልጋዮችን
በስተቀር የማይሰሙ። ከእግዚአብሔር
የሆነውንና ያልሆነውን ለመለየተ
ግድ በማይሰጣቸው አገልጋዮች ብቻ
ወደ ውድቀታቸው ያመራሉ አክአብ ያደረገው
ይህንኑ ነው። እንግዲህ አንባቢው
እንደነዚህ አይነት ክስተቶችን ሲመለከት
ልብ ሊል መንፈሱን ሊለይ ይገባዋል።
እኛ ከእግዚአብሔር
ነን እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል፡
ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም
በዚህም የእውነትን መንፈስና የሃሰትን
መንፈስ እናውቃለን። 1ኛ ዮሃንስ 4፡6
እንግዲህ ለማጠቃለያ ያህል
እግዚአብሔር ዛሬ ሊገልጽልን የወደደው በህይወታችን እግዚአብሔር
ያየልን በቃሉም የተናገረልን ቦታ
እንዳንደርስ ዛሬ በተለያየ አሰራር
ሊያጓትተንና ቢችልም ሊያስቀረን
የሚፈልገውን አሰራር እንደ ኤልዛቤል መንፈስ ያለውን መቃወም
ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ኤልዛቤል ወደ
ቤተክርስቲያን የገባችበትን አሰራር
ለይቶ ማፈራረስ ነው። በዚህም እንደ
እግዚአብሔር ፈቃድ ያልሆነ ጋብቻን
በማፋታት (እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ
ያልሆነ መንፈሳዊ ቁርኝት) አግዚአብሔር
ለሚወደው ጋብቻ ራስን ፈቃድን ሁሉ
አሳልፎ መስጠት ነው እርሱም እግዚአብሔር
በመንፈሱ አማካኝነት በኛ ውስጥ ይገኛልና
በእርሱ መመራት በቃሉ መኖር ነው።
ከመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተነሳም
እግዚአብሔር በአገልጋዩ ሁሉ ላይ
ሲሰራ ማንም ሊቋቋመው ወደ
ማይችል ክርስቶስ ወደ ተናገረለት
የአካል አንድነት መምጣት እንችላለን።
ዛሬ እግዚአብሔር በነብያትና
በሓዋርያት አንደበት እየተናገረ
ያለውን የአንድነት እነጻ የፍጻሜ
ስራ እንዳንሰራ አላሳልፍ ብሎን ካለው
በራሳችንና በስሜታችን ከፋፍለን
ከያዝነው የተለያየ ምክንያት እየሰጠን
በጥቅስም እያስደገፍን ከምናጠፋው
ጊዜ እንውጣ፣ ወደ ትክክለኛው መንገድ
እንውጣ፣ በዙሪያችን እራሳችን ከፈጠርናቸው
መሰናክሎች እልፍ እንበል። ከዶክትሪንና
ከዲኖሚኔሽን ግድግዳ እንለፍ። የቀመር
ጉዞ እናቁምና ጌታ ሆይ ዛሬ እንዴት
እንድሄድ ትወዳለህ ብንል ጥበብ ነው።
እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ ይወዳል
ስለዚህም አንድ ልጁን እስከ ሞት ኣሳልፎ
ሰጠ
እግዚአብሔር በማስተዋል፣ በጥበብና በመገለጥ መንፈስ እጅግ አብዝቶ ይባርካችሁ
ወንድም ዳንኤል መኮንን