Thursday, February 28, 2013

የሰነበተ ዜና በሰበር፦ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ፮ኛው ፓትርያርክ ሆኑ

ብፁዕ አቡነ ማትያስ በ500 ድምዕ

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ98 ድምፅ
 ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል70 ድምፅ
 ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ98 ድምፅ
 ተመራጩ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ
 በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ማትያስ የካቲት 24 ቀን 2005 . በመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሚሾሙ ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ይኾናሉ፡- ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያሪክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት !!!
 በዛሬው የመራጮች መዝገብ 808 መራጮች ተመዝግበዋል፡፡  806 መራጮች መርጠዋል፡፡
 15 ድምፆች ዋጋ አልባ ኾነዋል፡፡ አንድ ባዶ የድምፅ መስጫ ወረቀት ተገኝቷል፡፡
 ተመራጩ ፓትርያሪክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ ንግግር አድርገዋል፡፡
 ለምርጫው በአጠቃላይ ብር 3,650,000 ወጪ መደረጉን የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ተናግረዋል፡፡

Wednesday, February 27, 2013

ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር! ማስለቀቂያ ካልተከፈለ – ኩላሊት ለገበያ

www.goolgule.com
     የጽሁፍ ምንጭ፤ ጎልጉል የድረ ገጽ ጋዜጣ                                                                                

አቧራ ይጨሳል። ከዚያ ያፈኑትን ይዘው ይሰወራሉአስደንጋጩ ታሪክ ውስጥ ያለው ስዕላዊ ገለጻ ነው። አንድ ወቅት አዲስ አበባ የህጻናት ሌቦች ተበራክተው ነበር። በወቅቱ በርዳታ ስም ተመዝግበው የፈጣሪ ስም እየጠሩ ህጻናትን በመነገድ የከበሩ ወረበሎች በደንብ የተደራጁና የሚቀናቀናቸውን የማስወገድ አቅም ስለነበራቸውአቧራው ጨሰየሚል ስያሜ የኮድ ስም ተሰጥቷቸው ነበር። አሁንም አሉ።ህጻን እናሳድጋለንእያሉ በዘረጉት ሰንሰለት የህጻናትን ደም የሚጠጡአንቱየተባሉ ሰዎች!! የውጪ አገር ዜጎች ጭምርበሱዳን ሰዎችን በማፈን ሲና በረሃ የሚሰውሯቸው ራሻይዳዎች የተደራጁ ናቸው። ከአረብ ምድር የፈለሱ ናቸው የሚባልላቸው እነዚህ ጎሣዎች በሱዳንና በኤርትራ የሚገኙ ሲሆን በተለይ በኤርትራ ያሉቱ ከዘጠኙ ጎሣዎች መካከል የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ አኗኗራቸው የዘላን በመሆኑ ከኤርትራ መንግሥት ቁጥጥር ውጪ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ እነዚህ ጎሣዎች እጅግ አሰቃቂ የሆነ የአፈናና የጭከና ድርጊት ሲፈጽሙ በወጉ ታጥቀውና ዘመናዊ ተሽከርካሪ በመያዝ ነው። የሚታፈነውን ሰው ከተቆጣጠሩ በኋላ አዋራ ይነሳል። የሚከንፉበት ተሽከርካሪ አሸዋውን ተርትሮት ሲወረወር የሚነሳው ጭስ ሲበተን እነሱ የሉም። ቀሪው ተግባርሚስትህን፣ ወንድምህን፣ እህትሽን፣ ዘመድሽን ለሚያርዱ የሰውነት ክፍል ሌቦች አሳልፈን ሳንሰጥ ዶላር ክፈል ወይም ክፈይየሚለው ድርድር ነው። ይህ ድራማ መሰል ንግድ ሲከናወን ተገደው ይሁን የንግዱ ተባባሪ በመሆን በውል በማይታወቅ ሁኔታ የድርድሩ አስተርጓሚ ሆነው የሚሰሩት ኤርትራዊያን እንደሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊያኖችም አሉበት ይባላል። ማንም ይስራው ማን ድርጊቱ አሰቃቂ መሆኑ ብዙዎችን አስለቅሷል። አስጨንቋል።
በደላሎች እስራኤል ለመግባት ጉዞ ከጀመሩት ወገኖች መካከል ስንቶቹ በሲና በረሃ ሟምተው እንደቀሩ መረጃ የለም። ከሱዳን ምድር ወጥተው ግብጽ በመሻገር ሲና በረሃ እንደ ከብት ተበልተው የሚጣሉት ወገኖች ስቃይ ለሰሚው ግራ ነው። ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው አሰቃቂ መከራ ከቀን ቀን እየተባባሰ ነው። አሰቃቂ ዜናዎች መስማት ለየእለቱ የሚያስፈልገን መሰረታዊ ጉዳይ እስኪመስል ተለመዷል። ይህ አሳሳቢ ጉዳይእስከመቼ በዚህ ይቀጥላልየሚለው የሁሉም ወገንዳር ቋሚዎችጥያቄ ነው።
ለጆሮ የሚሰለች ነው፣ እርዳታ መስጠት ታከተን፣ የሚል መልስ የሚሰጡ አጋጥመውኛል። ድርጊቱ ተደጋግሞ ለጆሮ የሚያሰለች ደረጃ እስኪደርስ እነዚህ ወገኖች የት ነበሩ? ቢያንስ ሌሎች ላይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይደርስ ምን ሰሩ? በውጪ አገር ያለን ወገኖች የሚረዳውንና የማይረዳውን መለየት የተሳነን ይመስለኛልበማለት በሚኔሶታ የሚኖሩት / ሰብለ አስተያየታቸውንና ተማጽኗቸውን ያሰማሉ።
የካቲት 32005 (2/10/2013) የቪኦኤ አማርኛ ክፍለ ጊዜ ያሰማው እረፍት የሚነሳ ዜና እስካሁን አልተቋጨም። ሱዳን ሸገራብ በሚባለው ሰፊ የስደተኞች ጣቢያ ከባለቤታቸውና ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩ / ትዕግስት ገብሬ ጥር 22 ቀን 2005 ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ከቤታቸው ይወጣሉ። በካምፕ ውስጥ ከሚገኘው ቤታቸው ወጥተው በግምት ሰላሳ ሜትር ሳይርቁ ታፈኑ።

ቀልድ እንደ እውነት!

 ከጥበበ ሲራክ ዘጉንዳጉንዶ


ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ  ማ…………ቴዎስ        
                           
                            ………….ትያስ


ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም፤ ወእጨጌ ዘመንበረ ተ/ሃይማኖት መልካም የሥራ ጊዜ  እንዲሆንልዎ እንመኛለን።

ቀልደኞች እንደእውነት ሲያደርጉት ለእኛስ መልካም ምኞት አይከለከልም አይደል?

Tuesday, February 26, 2013

ለነ አባ እንቶኔ!!


እመሰ አማን ጽድቀ ትነቡ...


ይድረስ ለነ አባ እንቶኔ፦(geezonline.org)


ሰላም ለክሙእንዳልላችኍ፤ እንደ እኔ ያለ አንድ ምስኪን እንደ እናንተ ላሉ ታላላቆች ከታች ወደላይ ሰላምታ ማቅረብ የማይገባው መስሎ ስለሚታያችኍ፤ ላስቀይማችኍ አልሻምና ይቅርብኝ።ሰላምክሙ ይብጽሐኒብየ እንዳልማጠናችኍም፤ ስንኳን ለሌላ የሚተርፍ ለራሳችኍ የሚበቃ ሰላም እንደሌላችኍ እያየኍ የሌላችኍን ነገር በመለመን እንዳሳቅቃችኍ ኅሊናየ አይፈቅድልኝም። ስለዚህ የሰላምታን ነገር በዚሁ እንለፈው።   

ሰላምታውን በዚሁ ካለፍነው ዘንድ ነገሬን በቀጥታ ልጀምር። ከቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ባገኘኹት ላይ ተመርጉዤ። በሊቃውንት ቋንቋ እንድገልጠው ከፈቀዳችኹልኝ፦ ጳጳሳት አይደላችኍ? ከብሉይ ታሪክ ምሳሌ አምጥቼ ግሥ ልገሥሥላችኍ ነው።

ርግጥ ነው ብዙዎቻችኍ ትርጓሜ መጻሕፍትን በወንበር ተምራችኋል ብየ አላስብም። እውነት ለመናገር ከመካከላችኍ አንዳንዶቹ ተነሹን ከወዳቂ፥ እሚጠብቀውን ከሚላላው፥ በፍቅደት የሚነበበውን በውኅጠት ከሚነበበው በሚገባ ለይታችኍ ማወቃችኍን ስንኳ እጠራጠራለኍ። አዛኜን። ይኹን እንጂ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ እንዲሁም የዐጤ ኀይለ ሥላሴ ስም አጠራራቸው የተመሰገነ ይኹንና አቡኑ አእምሮ፥ ንጉሡ ገንዘብ ኾነው በረድኤተ እግዚአብሔር ያሳተሙትን የዳዊት አንድምታ ከመጽሐፍ መደርደሪያችኍ ፈላልጉና (ድንገት ለነ አቦይ መልእክት ስትፋጠኑ ጊዜ አላደርስ ብሏችኍ እስከዛሬ ያልገዛችኹት ከኾነም፤ ስንኳን አንድ መጽሐፍ አገር ምድሩን የሚገዛ ገንዘብ በየባንክ ቤቱ ስለሞላችኍ ዛሬውኑ ልካችኍ አስገዙና) የምገሥሥላችኍ ግሥ ተስማሚ መኾን አለመኾኑን አረጋግጡ።

የምተኩረው በዳዊት መዝሙር ላይ ነው። 57ኛው። ትርጓሜው የመቃብያንን ታሪክ ያስተርካል። ከታሪኩ አኹን የያዝነውን መዝሙር ለመረዳት የሚያሻው ክፍል፦ ስምዖን፥ እልፍሞስ፥ መባልስ የተባሉ ሦስት ንኡሳን ካህናት ለሹመት ሲሉ እስራኤልን የአሕዛብ ንጉሥ አንጥያኮስ እጅ እንዲያደርጋት መምከራቸውን፤ እሱ ስንኳአኹን የተናገራችኹትን ነገር ሳላስበው ውየ ዐድሬ አላውቅም። ነገር ግን እስራኤል ሰዎቹ ጽኑዓን ናቸው፤ አምባቸውም ጽኑ ነው ሲሉ እሰማለኍ። ፈጣሪኣቸውም ይረዳቸዋልና መቅረቴ ስለዚህ ነው እንጂ።ቢላቸው፤እኛ ባወቅነ እናስገባኻለን። አንተም አመንኍ ብለኽ ዐዋጅ ነግረኽ ምስዋዕተ እሪያውን በዃላ በዃላ እያስጎተትኽ ላሙን በጉን በፊት በፊት እያስነዳኽ ብለው መክረውት ኺደው የከተማዋን ቅጥርክፈቱልንያሏቸውን ይመለከታል። በዚህም ምክንያት "ፈጣሪየ የሃይማኖት አብነት ቢያደርገኝ የክህደት፥ የጥብዓት አብነት ቢያደርገኝ የፍርሃት፥ የበጎ አብነት ቢያደርገኝ የክፋት አብነት እኾናለኹን? አይኾንም" ያለው እውነተኛ ካህን አልዓዛር ሰባት ልጆቹ በሰይፍ ሲመቱ ሚስቱም በጡትና በጡቷ መኻል በኩላብ ተሰቅላ በሰይፍ ተቀልታለች። እሱም ይኽን ኹሉ እያየ ስንኳ ከጽናቱ የማይመለስ በመኾኑ በሰም የተጠማ የጋለ ብረት ምጣድ በራሱ ላይ ተደፍቶበት ተንጠቅጥቆ ሙቷል። በዚያኑ ጊዜ ከእስራኤል አራት ዕልፍ ዐብረው ዐልቀዋል፤ አራት ዕልፍ ተማርከዋል፤ አራቱን ዕልፍ ይሁዳ መቅብዩ እየተዋጋ ይዟቸው ወጥቷል። ስለዚህ በዚያን ጊዜ በሃይማኖታቸው የጸኑት ባባታቸው በመቃቢስ መቃብያን ተብለዋል። ዕጉሣን በስደት ጽኑዓን በምግባር ወበሃይማኖት ማለት ነው።